Quantcast
Channel: ተሟገት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

በመሬት ይዞታ አስተዳደር ቢሮዎች የደኅንነት ካሜራዎች ሊገጠሙ ነው

$
0
0

በአዲስ አበባ ከተማ አሥሩም ክፍላተ ከተሞች የመሬት ይዞታ አስተዳደር ቢሮዎች የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስወገድ፣ እንዲሁም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የደኅንነት ካሜራዎች ሊገጠሙ ነው፡፡

ከደኅንነት ካሜራዎች በተጨማሪ ከመሬት ይዞታ ጋር የተገናኙ ፋይሎችን ወደ ዲጂታል ሰነድነት በመቀየር፣ የፋይል ስርቆትን በማስቀረት ውጤታማ አገልግሎት መስጠት በፕሮጀክቱ ውስጥ መካተቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ለሙ ገመቹ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከመሬት ይዞታ ጋር የተገናኙ የሙስና ድርጊቶችን ሰዎችን በማሰር ብቻ መቅረፍ የማይቻል በመሆኑ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው፡፡

ይህንን የቁጥጥርና አገልግሎት የማቀላጠፍ ሥርዓት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የመሬት ይዞታ ቢሮዎች ለመትከል፣ የ25 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ እንደቀረበ ገልጸዋል፡፡

ቴክኖሎጂው ደንበኞች በአንድ ሥፍራ ሆነው አገልግሎት አግኝተው የሚመለሱበትን ሥርዓት የሚፈጥርና በዲጂታል ሥርዓት ወረፋ የሚያስይዝ በመሆኑ፣ ግርግርን እንደሚያስቀርና አቅም ባላቸውና በደላሎች ሲመራ የነበረውን ብልሹ አሠራር የሚያፈርስ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በመሬት ይዞታ አገልግሎት ቢሮዎች 17 ዓይነት አገልግሎቶች የሚሰጡ እንደሆነና ከእነዚህም መካከል የይዞታ ማቀላቀል፣ የይዞታ አገልግሎት ለውጥ፣ ካርታ፣ ስም ዝውውር፣ የንብረት ግምት፣ የቤት ተመንና የካርታ ሕጋዊነት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

Trending Articles