ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ያቀረቧቸው ዕጩዎች ሹመትን ፓርላማው ዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም አፀደቀ፡፡አቶ ዳኜ መላኩ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡
በመሆኑም አቶ ዳኜ መላኩ መሀሪ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን የተሾሙ ሲሆን አቶ ፀጋዬ አስማማው ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡
በዚህ መሠረትም አቶ ዳኜ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህን የተኩ ሲሆን አቶ ፀጋዬ አስማማው ደግሞ በጡረታ የሚሰናበቱትን አቶ መድህን ኪሮስን ከዛሬ ጀምሮ ተክተው ይሠራሉ፡፡
በምሥሉ መሀከል ላይ የሚታዩት አቶ ዳኜ መላኩ ሲሆኑ፣ በቀኝ በኩል ደግሞ አቶ ፀጋዬ አስማማው ናቸውበምሥሉ መሀከል ላይ የሚታዩት አቶ ዳኜ መላኩ ሲሆኑ፣ በቀኝ በኩል ደግሞ አቶ ፀጋዬ አስማማው ናቸው
Standard (Image)
