Quantcast
Channel: ተሟገት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ድጋፏን ቀጥላለች

$
0
0

‹‹ኢትዮጵያ ለአኅጉሩም ሆነ ለዓለም ሰላም ወሳኝ ሚና እየተጫወተች ነው››  አምባሳደር ሱዛና ሙርሔድ፣ በኢትዮጵያ የብሪታኒያ አምባሳደር

ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ የምትሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ የብሪታኒያ አምባሳደር ሱዛና ሙርሔድ ይህን የገለጹት፣ በብሪታኒያ ድጋፍ የፌዴራል የሰላም ድጋፍ ማሠልጠኛ ማዕከል የአጭር ጊዜ ሥልጠና የወሰዱ ሠልጣኞችን የካቲት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለሆኑት ብሪታኒያና ኢትዮጵያ፣ ዓለም አቀፍ የሰላምና የፀጥታ አጀንዳ ቅድሚያውን እንደሚይዝ የብሪታኒያ ኤምባሲ ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል፡፡ ይህም 60 በመቶ ግጭቶች በሚፈጠሩበትና 90 በመቶ የሰላም ማስከበር ወጪ በሚወጣበት አፍሪካ ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆነ መግለጫው ያክላል፡፡

ብሪታኒያ የአፍሪካ ተቋማት ግጭቶች እንዲቀንሱ፣ በአግባቡ እንዲያዙና እንዲቀረፉ ለማድረግ በጋራ እንደምትሠራም ተመልክቷል፡፡ ለዚህም ከአፍሪካ ኅብረትና ከአካባቢያዊ የጋራ የኢኮኖሚ ማኅበረሰቦች ጋር በመሥራት፣ በአኅጉሪቱ የሚከናወኑ የሰላም ማስከበር ጣልቃ ገብነቶች አቅምን ለማጎልበትና ወጥነት ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት እንደሚጨምርም ተጠቅሷል፡፡

አምባሳደር ሙርሔድ፣ ‹‹ዓለም አቀፍ ሰላምና ፀጥታ ለብሪታኒያና ለኢትዮጵያ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ብሪታኒያ በአውዳሚነታቸው አቻ የማይገኝላቸውን ግጭቶች ለማቆም ድጋፍ የማድረግ ዓላማ አላት፡፡ የተመድንና የአፍሪካ ኅብረትን የመደገፍ ረዥም ታሪክም አለን፡፡ ኢትዮጵያ ለአኅጉሩም ሆነ ለዓለም ሰላም ወሳኝ ሚና አላት፡፡ ለተመድና ለአፍሪካ ኅብረት በርካታ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ወታደሮቿን በማዋጣት ትልቅ ጠቀሜታ እየሰጠች ነው፡፡ ብሪታኒያ ኢትዮጵያን ብቃት ያላት አጋር እንደሆነች ነው የምትወስደው፡፡ ኢትዮጵያ ደረጃዎቹንና አፈጻጸሟን እንድታሻሽል የምታደርገው ዕርዳታ የተመድና የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮዎችን እንደሚጠቅምም እምነታችን ነው፤›› ብለዋል፡፡

ብሪታኒያ የኢትዮጵያን የፀጥታ ዘርፍ ለረዥም ጊዜ ስትደግፍ መቆየቷ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በመጥቀስ ይህን ድጋፍ እንድታቋርጥ ከተለያዩ አካላት ጫናዎች መደረጋቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ ተፅዕኖ ጋር በተገናኘ በሚመስል ሁኔታ የተወሰኑ ድጋፎች ሳይቋረጡ ወደ ሌሎች ፕሮጀክቶች እንዲሸጋገሩ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ በተለይ ድጋፎቹ በንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ በጤና፣ በትምህርትና ተጓዳኝ በሆኑ መስኮች ላይ የተወሰነ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡ 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

Trending Articles