Quantcast
Channel: ተሟገት
Viewing all 1275 articles
Browse latest View live

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክን ሊጎበኙ ነው

$
0
0

የኛ ለተባለው ፕሮጀክት የሬዲዮ ፕሮግራም ይለቀቅ የነበረው ፈንድ እንዲቋረጥ የወሰኑት የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው፡፡

ከያዟቸው የጉብኝት ዕቅዶች መካከል ሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ እንደሚገኝበት የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትሯ ፕሪቲ ፓቴል የኛ ለተባለው የሬዲዮ ፕሮግራም ይለቀቅ የነበረው 5.2 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲቋረጥ ያደረጉት በቅርቡ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ሚኒስትሯ ፈንዱ ያቋረጠበት ምክንያት መንግሥታቸው ከዕርዳታ የተለየ መንገድን እንደሚመርጥና ይህም ዓለም አቀፍ የንግድ ትብብርን ማበረታት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኛ ለተባለው የሬዲዮ ፕሮግራም ፈንድ እንዲቋረጥ ካደረጉ በኋላ የሐዋሳ የኢንዱትሪ ፓርክን በዚህ ሳምንት እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡

ሚኒስትሯ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔን እንደሚከታተሉ፣ ከጉባዔው ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዶ/ር ወርቅነህ ገበየውን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚያነጋግሩ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ቀጥሎ ትልቁን የእንግሊዝ ዕርዳታ የምታገኝ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2015 ብቻ 334 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡  

Standard (Image)

የደሴውን ሼክ ኑሩ ይማም መግደላቸው ተረጋግጦባቸዋል የተባሉ ተከሳሾች ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው

$
0
0

በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጊድ አካባቢ ሰኔ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ሼክ ኑሩ ይማምን መግደላቸው በሰነድና በሰው ማስረጃዎች ተረጋግጦባቸዋል የተባሉ ተከሳሾች በጽኑ እስራት እንዲቀጡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጠ፡፡

ሼክ ኑሩን በመግደል ተከሰው የነበሩት ይመር ሁሴን ሞላ በ16 ዓመታት፣ አህመድ እንድሪስና ሳሊህ መሀመድ እያንዳንዳቸው በ15 ዓመታት፣ ዑመር ሁሴን አህመድ በ15 ዓመታት ከስድስት ወራት፣ ኢብራሂም ሙሔ በ14 ዓመታት፣ አንዋር ዑመር ሰይድ በ12 ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ሌሎቹም ተከሳሾች ከሦስት ዓመታት እስከ አምስት ዓመታት በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ ሲመረምሩ የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቅጣት ውሳኔው እንደገለጸው፣ ፍርደኞቹ ያስያዙዋቸው ኤግዚቢቶች በሙሉ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑና በወንጀል ሕግ አንቀጽ 12 እና ተከታታይ ድንጋጌዎቹ አንፃር ፍርደኞቹ ከማንኛውም ሕዝባዊ መብቶቻቸው ለሁለት ዓመት መታገዳቸውን በውሳኔው ገልጿል፡፡

በፍርደኞቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀና ለ)፣ 38(1)ን እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)፣ 6 እና 7ን በመተላለፍ ሼክን ኑሩን መግደላቸውን ዓቃቤ ሕግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ሲያረጋግጥ፣ እነሱ ባቀረቧቸው የመከላከያ ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻላቸው ታኅሳስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ጥፋተኛ መባላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Standard (Image)

በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ዋስትና ተፈቀደላቸው

$
0
0

የኢትዮ ቴሌኮም ከሚገዛቸው ተሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ በመንግሥት ላይ ኪሳራ እንዲደርስ አድርገዋል በሚል በሙስና ተጠርጥረው ከ15 ቀናት በፊት ታስረው የነበሩት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ሥራ አስፈጻሚና ሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ዋስትና ተፈቀደላቸው፡፡

ምክትል ሥራ አስፈጻሚና ሶርሲንግና ፋሲሊቲ ዲቪዥን ኃላፊ አቶ አብርሃም ጓዴና የሥራ ባልደረቦቻቸው አቶ ፍስሐ ሹመት፣ ፍሬዘር በኃይሉ፣ ልዑል መንበሩ፣ ሰለሞን ግርማ፣ ቴዎድሮስ ተስፋዬ፣ ዓለማየሁ ግርማና ዮሐንስ አውግቸውን ጠርጥሮ ለእስር ያበቃቸው ፌዴራል ፖሊስ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከከረዩ ቱር ኤንድ ትራቭል ድርጅት ጋር 67 ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ከተፈጸመ ውል ጋር በተያያዘ ሙስና ፈጽመዋል በማለት ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የምርት ዘመናቸው እ.ኤ.አ. 2000 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ከከረዩ ቱር ኤንድ ትራቭል ለመግዛት ውል የፈጸመ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪዎቹ ከአቅራቢው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ሐጐስ ጋር በጥቅም በመመሳጠር የምርት ዘመናቸው እ.ኤ.አ. ከ2000 በታች የሆኑ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ በማድረጋቸው፣ በመንግሥትና በተቋሙ ላይ ከ343 ሺሕ ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቶ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ለጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶት ነበር፡፡

ፖሊስ በዕለቱ ቀርቦ የሠራውን ካስረዳ በኋላ የሚቀረው ምርመራ እንዳለው በመግለጽ ተጨማሪ 14 ቀናት ጠይቆ ነበር፡፡ የጊዜ ቀጠሮውን የፈቀደው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ግን የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፣ ለተጠርጣሪዎቹ ዋስትና በመፍቀድ መዝገቡን ዘግቶታል፡፡ በመሆኑም የከረዩ ቱር ኤንድ ትራቭል በ50,000 ብር፣ የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በ20,000 ብርና ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ10,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን ሲሰጥ መርማሪ ፖሊስ ይግባኝ እንደሚል በማመልከቱና በተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓት የማስረጃ ሕግ 434 አንቀጽ 5(2) መሠረት መርማሪው በአምስት ቀናት ውስጥ ይግባኝ ያለበትን ማስረጃ እስከሚያቀርብ፣ ተጠርጣሪዎቹ በእስር ቆይተው የይግባኝ ማስረጃው ካልቀረበ ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. 8፡00 ሰዓት ላይ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡   

 

Standard (Image)

አቶ አስፋው ተፈራ ወልደመስቀል (1921 - 2009)

$
0
0

ኢትዮጵያ የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራን (1928 - 1933) በድል ከቀለበሰች በኋላ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማቆም፣ አገሪቱን በየዘርፉ ለማጠናከር በተደረገው የመጀመሪያዎቹ የ15 ዓመታት ጉዞ ውስጥ በተለይ በትምህርት መስክ አስተዋጽኦ ካደረጉት ኢትዮጵያውያን መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በ1948 ዓ.ም. ያወጣው የተሻሻለው ሕገ መንግሥት ከመተግበሩ በፊት በነበሩት ዓመታት፣ የትምህርትና የሥነ ጥበብ ሚኒስቴር የአገሪቱን ኦፊሲያል ቋንቋ አማርኛን በትምህርትና በሥነ ጽሑፍ ለማበልፀግ እንዲያመች ሲንቀሳቀስ ከተሰለፉት አንዱ፣ በ1945 ዓ.ም. በአማርኛ ትምህርት የበሰሉ በተለይም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን በብዛት ማግኘት ባልተቻለበትና በአማርኛ ትምህርት አሰጣጥ ችግርን ለማስወገድ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልዩ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎችን በመመልመል ለማስተማር ከተመደቡትና ለፍሬ ካበቁት መካከል አንዱ አቶ አስፋው ተፈራ ነበሩ፡፡

በ1942 ዓ.ም. በመምህራን ማሠልጠኛ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት አቶ አስፋው፣ በደብረ ብርሃን ኃይለማርያም ማሞና በአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስተማሪነታቸው በተጨማሪ ለሦስት ዓመታት በተከታታይ የክረምት የማሻሻያ የአማርኛ ኮርስ ለመምህራን ሰጥተዋል፡፡

በጣሊያንኛና በፈረንሣይኛ ቋንቋዎች የተከበበው አማርኛ በአገር ልጆች ጎልቶ እንዲወጣ፣ የመማርያም የሥራ ቋንቋም ሆኖ እንዲገኝ ይጥር የነበረው የትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴርን ተግባር ያከናውኑ ነበር፡፡

በ‹‹እኔ ማን ነኝ?›› እንደተጻፈው በአገር ፍቅር ስሜት ቀስቃሽ መዝሙሮችም የታጀበ ነበር፡፡

‹‹ለእምዬ ኢትዮጵያ ለውድ አገራችሁ፣

ተግታችሁ ተማሩ ልጆች እባካችሁ

ያልተማረ ዜጋ ደንቆሮ ሆናችሁ

የሌላ አገር ዜጋ እንዳይወስዳችሁ፡፡››

አቶ አስፋው ከአስተማሪነታቸው በተጨማሪ የብሔራዊ ዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና ባህል ድርጅት) የድርሰት ክፍል በኃላፊነት መሥራታቸው ለደራሲነትም ለተርጓሚነትም በር ከፍቶላቸዋል፡፡

በሀገረ እንግሊዝ በትምህርት አስተዳደር ከፍተኛ ትምህርት (1948-50 ዓ.ም.) ከተከታተሉ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ክፍል በሕዝብ አስተዳደር ዘርፍና ከዚያም በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በመዘዋወር አጫጭር ኮርሶችን ሰጥተዋል፡፡

በ1951 ዓ.ም. በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ በባሕር ክፍል የወደብ አስተዳደር የሠራተኛ ማስተዳደሪያና ማሠልጠኛ ክፍል ሹም በመሆን፣ ከሦስት ዓመት በላይ በዋናው መሥሪያ ቤትና በምፅዋና አሰብ ቅርንጫፎች ያገለገሉት አቶ አስፋው፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የነበራቸው የአገልግሎት ቆይታ ያበቃው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጥረው በሌጎስ (ናይጄሪያ) የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሦስተኛ ጸሐፊ በመሆን እስከ 1956 ዓ.ም. ካገለገሉ በኋላ ነበር፡፡

ከሦስት ዓመት ተመንፈቅ የዲፕሎማሲ ሥራ ቆይታ በኋላ በልጅነት ተጀምሮ ወደነበረው የንግድ ሥራ ሲመለሱ የጽሕፈት መሣሪያ መደብር፣ ቼምበር ማተሚያ ቤትንና ኢምፔሪያል ሆቴልን በማቋቋም ከ50 ዓመታት በላይ ስኬታማ ሕይወት መምራታቸው ይወሳል፡፡

አቶ አስፋው የግል ማተሚያ ቤት ለማቋቋምና ወደ ሙያው ለመግባት ከገፋፉዋቸው ምክንያቶች መካከል ሥነ ጽሑፍ መውደዳቸው፣ ለንደን በትምህርት ላይ በነበሩበት ጊዜ በትርፍ ሰዓት ዩናይትድ ፕሬስ ውስጥ መሥራታቸው ይጠቀሳሉ፡፡ በዘመነ ዲፕሎማትነታቸው በሌጎስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አጠገብ የነበረው ሪብዌይ ፕሪንተርስ “Africa’s March to Unity” የተባለው መጽሐፋቸው የታተመበት ሲሆን፣ ወደ ኅትመት ሕይወት እንዳቀረባቸው በግለ ታሪካቸው ገልጸውታል፡፡

የግላቸው የሆነው ማተሚያ ቤታቸው መጀመሪያ በ1958 ዓ.ም. የተቋቋመበትና ሥራውን የጀመረው በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት (ኢትዮጵያን ቼምበር ኦፍ ኮመርስ) ሕንፃ ምድር ቤት ውስጥ ሲሆን፣ ስሙንም ‹‹ቼምበር›› ያሉት ንግድ ምክር ቤቱ ማተሚያ ቤቱን ለማቋቋም ባደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍና ትብብር የተነሳ ስሙን በታሪካዊ ማስታወሻነቱ ለማሰብ መሆኑን በግለ ታሪካቸው ጠቅሰውታል፡፡

አቶ አስፋው በማኅበራዊ ሕይወታቸው በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሙያና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ በአባልነትና በኃላፊነት መሥራታቸውን ገጸ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

ከግማሽ ክፍለ ዘመን ባለፈ ጊዜ በአንጋፋ የብዕር አዛውንቶች በእነ አቶ አበበ ረታ፣ ራስ ቢትወደድ መኰንን እንዳልካቸውና ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት በተቋቋመው የኢትዮጵያ የድርሰት ማኅበር የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል፣ በ1972 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ደራስያን አንድነት ማኅበር (ኢደአማ) ተብሎ በአዲስ መልክ ሲቋቋም ገንዘብ ያዥና ንብረት ጠባቂ ነበሩ፡፡ በአዲስ አበባና በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤቶችም በአመራር ቦርድ ውስጥም አገልግለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የላየንስ ክለብ በማቋቋምና በመምራት ለኬንያ፣ ለኡጋንዳ፣ ለታንዛኒያ፣ ለሲሼልስና ለኢትዮጵያ ላይንስ ክለብ በምክትል ገዢነት ለ15 ዓመታት መሥራታቸውም ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊትና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በጋራ የተቋቋመው የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አሰፋው፣ ለቤተ ክርስቲያን ካበረከቱት አገልግሎት በመነሳት የአዲስ ዓለም ርዕሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ‹‹ብላታ ጌታዬ›› የሚል የክብር ስም ከካባው ጋር ሰጥታቸዋለች፡፡

በኢትዮጵያ የግል ፕሬስ ታሪክ ውስጥ የሚጠቀስ ‹‹ዕድሜ›› የተሰኘ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት በየጊዜው ያሳትሙ የነበሩት አቶ አስፋው፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ለትምህርት የሚሆኑ ግለ ታሪክና በኢትዮጵያና በአፍሪካ ታሪኮች ላይ የተመሠረቱ 14 መጻሕፍትን ደርሰውና ተርጉመው ለንባብ አብቅተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል መክስተ ሰዋስው (የአማርኛ ሰዋስው)፣ ሰንደቅ ዓላማችን፣ ዶን ኪሾት አንደኛ መጽሐፍ፣ እኔ ማን ነኝ? የዕድሜ ውሎ ማስታወሻ፣ “Africa: Past, present and Future Development Panorama of Historical Revolution” ይገኙባቸዋል፡፡ ለኅትመት የተዘጋጁ ‹‹ዳንቴ አልጊሪ››ን ጨምሮ አሥር መጻሕፍት አሏቸው፡፡ ለዚህም 75ኛ ዓመት ልደታቸውን ባከበሩበት ወቅት ከቀረበው ግጥም አንዱ አንጓ ለጥቅስ ይበቃል፡፡

‹‹ሆኛለሁ ደራሲ ታሪክ ጂኦግራፊ፣

እንዲሁም ከታቢ ልቦለድ ጸሐፊ፡፡

ነበርኩኝ አርታኢ ገጣሚ ተርጓሚ፣

ለሀገሬ ልጆች በሚሆን ተስማሚ፡፡››

ከስድስት ዓመት በፊት እንደጻፉትም፣ ‹‹የሰው ልጅ ጥሮ ግሮ እንዲበላ ወደዚህች ዓለም ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የሚያጋጥሙትን ውጣ ውረዶች እያሳለፈ ያልፋል፡፡ የዕድሜው እርከን እስከሚቋጭበት ድረስ ዘመኑ ሁሉ የድካምና የፈተና ነው፡፡ በመሆኑም የምድሩን ሩጫ ፈጽሞ የኑሮ ምዕራፉን ከመዝጋቱና ወደ ፈጣሪው ከመጓዙ በፊት ለሚተካው ትውልድ ታሪኩን ጽፎ መተው ተገቢ ስለሆነ፣ እኔም ለቤተሰቤና ለወዳጆቼ ለሚያውቁኝም ጭምር ይህንን የሕይወት ጉዞዬን ማስታወሻ አዘጋጀሁ፤›› ብለው ሞትን ቀድመውት ግለታሪካቸውን ለኅትመት ብርሃን አብቅተውታል፡፡

ይሁን እንጂ ባደረባቸው ሕመም ረዘም ላለ ጊዜ በአገር ውስጥና በውጭ አገር በሕክምና ሲረዱ የቆዩት አቶ አስፋው፣ ሰኞ ጥር 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በተወለዱ በ88 ዓመታቸው አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው በቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል በሁለተኛው ቀን ተፈጽሟል፡፡

ከአባታቸው ከአቶ ተፈራ ወልደመስቀልና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ካብትይመር ቅዳሜ ሚያዝያ 12 ቀን 1921 ዓ.ም.፣ በቀድሞ አጠራሩ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት፣ ጨርጨር አውራጃ በጭሮ ወረዳ፣ ጎርቆሬ በተባለ መንደር የተወለዱት አቶ አስፋው፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሰበ ተፈሪ (ጭሮ) ከተማ በደጃች ወልደገብርኤል አባሰይጣን፣ በአዲስ አበባ ሊሴ ገብረማርያም፣ በተግባረ ዕድ ትምህርት ቤቶችና በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሲከታተሉ፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በለንደን የምሥራቅ አፍሪካ ትምህርት ቤት በ1951 ዓ.ም. በትምህርት አስተዳደር ተመርቀዋል፡፡ በዚያው ዓመት ከካናዳ ናሽናል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአፍሪካ ጥናት የመጀመሪያ ዲግሪን በመላላክ ትምህርት አግኝተዋል፡፡

አቶ አስፋው ተፈራ በ1953 ዓ.ም. ከወ/ሮ ጥሩወርቅ መንግሥቱ ወልደ ጻድቅ ጋር ሕጋዊ ጋብቻ በመፈጸም፣ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ከማፍራታቸውም በላይ አምስት የልጅ ልጆችንም አይተዋል፡፡

Standard (Image)

የሕግ ምርምር ሥልጠናና የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራምን የሚመራ ተቋም ሊመሠረት ነው

$
0
0

የፌዴራል መንግሥት የሕግ ምርምር፣ ሥልጠናና የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራምን በመቀላቀል በአንድ ተቋም ሥር አድርጎ ለመሥራት እየመከረ ነው፡፡ የመጀመሪያውን ምክክር ከባለድርሻ አካላት ጋር በሐርመኒ ሆቴል ጥር 15 ቀን 2009 ዓ.ም. አድርጓል፡፡

ለውይይት የቀረበው ረቂቅ የፖሊሲ ሰነድ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩትና የፍትሕ አካላት ባለሙያዎች የሥልጠና ማዕከልን በመቀላቀል፣ ‹‹የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት›› የሚል ስያሜ ያለው አዲስ ተቋም የመፍጠር ዕቅድ በመንግሥት ዘንድ እንዳለ ያሳያል፡፡ አዲሱ ተቋም የፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራሙንም እንዲመራ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ የተቋሙ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆንም ሰነዱ ይጠቁማል፡፡

የሚዋሀደው ተቋም ከሚኖሩት ሥልጣንና ተግባራት መካከል በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ጥናትና ምርምሮችን ማድረግ፣ የፍትሕና የሕግ መረጃ ማዕከል በመሆን ማገልገል፣ የፍትሕ አካላት አመራሮችንና ባለሙያዎችን በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በአመለካከትና በሥነ ምግባር በማነፅ የፍትሕ ሥርዓቱ ከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና ሥነ ምግባር፣ እንዲሁም ሕዝባዊ አመኔታና ተቆርቋሪነት ባላቸውና ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ መከበር በፅናት በሚቆሙ ባለሙያዎች የተገነባ እንዲሆን ማስቻልና የፍትሕ ሥርዓትና የሕግ ትምህርት ማሻሻያ ፕሮግራምንና ሌሎች በፍትሕ ዘርፉ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን በማቀናጀትና በመምራት ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 22/1990 በ1990 ዓ.ም. የተቋቋመ ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ የፍትሕና የሕግ ሥርዓቱን ብቁና ዘመናዊ ለማድረግ፣ ሕገ መንግሥቱን በተሟላ ሁኔታ ሥራ ላይ ለማዋል፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ለማፋጠንና የፍትሕ አካላትን አቅም ለመገንባትና ሥራቸውን ለማቀላጠፍ የሚረዱ ጥናትና ምርምሮችን ለማካሄድ፣ የሕግ ነክ መረጃዎችንና የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለማሳተምና ለማሠራጨት፣ እንዲሁም የፍትሕና የሕግ ሥርዓቱንና የሕግ ትምህርትና ሥልጠናን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍና ከዚሁ ጋር የተያያዙ ተግባራትን ለማከናወን የተቋቋመ ነው፡፡

የፍትሕ አካላት ባለሙያዎች የሥልጠና ማዕከል ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 364/1995 አማካይነት በ1995 ዓ.ም. የተቋቋመ ነው፡፡ የማዕከሉ ዓላማዎች ሕገ መንግሥታዊ ግንዛቤንና ባለቤትነት ማክበር፣ የላቀ የዳኝነት ሥርዓት ማረጋገጥ፣ ዳኞችና ዓቃቢያነ ሕግ የሙያ ብቃታቸውን በቀጣይነት እንዲያሻሽሉ ማድረግ፣ ሙያውን ለሚቀላቀሉ አዳዲስ ዳኞችና ዓቃቢያነ ሕግ የትውውቅ መድረክ ማዘጋጀት፣ ዳኞችና ዓቃቢያነ ሕግ ከአዳዲስ ሕጎችና አሠራሮች እንዲሁም ለሥራቸው አስፈላጊ ከሆኑ ሌሎች ዕውቀቶች ጋር እንዲተዋወቁ ማድረግ፣ ለፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም ባለቤትነት መፍጠር ናቸው፡፡

የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራሙ ደግሞ የተነደፈው ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን፣ ዓላማውም የአገሪቱን የፍትሕ ሥርዓት አስከፊ ገጽታ በመለወጥ በሚገባው ደረጃ የተሻሻለ የፍትሕ አገልግሎት እንዲገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው፡፡

መንግሥት እነዚህን እንቅስቃሴዎች በአንድ ተቋም ሥር ለማድረግ የተነሳሳው ተቋማቱ ሥራ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ተግባራትን ቢያከናውኑም፣ የሚጠበቅባቸውን ያህል ውጤታማ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እንደሆነ የውይይት ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ለዚህ አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብለው ከተጠቀሱ ችግሮች መካከል አደረጃጀት/መዋቅራዊ ተግዳሮት አንዱ ነው፡፡ ይህም በዋነኛነት ሁለቱ ተቋማት ተደራራቢና ተዛማጅ ኃላፊነቶችን በመያዛቸው የሚገለጽ ነው፡፡ የተቋማቱ ተጠሪነት በየጊዜው የሚለዋወጥና አሁንም ለተገቢ ተቋማት ተጠሪ መሆናቸው ጥያቄ የሚቀርብበት ጉዳይ መሆኑም እንደ ተጨማሪ ተግዳሮት ተጠቅሷል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡ ማዕከሉ ደግሞ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ ነው፡፡

በረቂቅ ሰነዱ ላይ ባለድርሻ አካላት ያቀረቧቸው የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከግንዛቤ ውስጥ ገብተው ከዳበረ በኋላ ተጨማሪ ውይይት ተደርጎበት፣ ተቋሙ በቅርቡ እንዲቋቋም የበላይ ባለሥልጣናት ፍላጎት እንዳላቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

Standard (Image)

መንግሥት ለፓርላማ አባላት መኖሪያ ቤት ውኃ መደጎሙ ከዓመታት በኋላ ጥያቄ አስነሳ

$
0
0

- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ 500 ሺሕ ብር ውዝፍ ዕዳ ተጠይቋል

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የሚያስተዳድራቸውን የመኖሪያ ቤቶች በአነስተኛ ዋጋ የተከራዩ የፓርላማ አባላት፣ የውኃ ፍጆታቸው በኤጀንሲው አማካይነት በመንግሥት ወጪ መሸፈኑ አግባብ አይደለም የሚል ጥያቄ ከዓመታት በኋላ ተነሳ፡፡

የቀድሞው የሥራ ዘመናትን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት ለተጠቀሙት የውኃ ፍጆታ፣ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 500 ሺሕ ብር እንዲከፈል መጠየቁን የኤጀንሲው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቡዕ ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በጠራው ስብሰባ፣ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የኤጀንሲውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል፡፡ በወቅቱ የውኃ ፍጆታ ጉዳይ አከራካሪ ከነበሩት ጉዳዮች ቀዳሚው ነበር፡፡

እንደ ኤጀንሲው ኃላፊዎች በተለይ ከ2005 ዓ.ም. በፊት በቤቶቹ ይኖሩ የነበሩት የምክር ቤት አባላት በያዙት ቤት የመኝታ ቤት ቁጥር ልክ ተሰልቶ ይከፍሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ አሠራር ተቀይሮ ለእያንዳንዱ ቤት ቆጣሪ እንዲገባላቸውና እንደየፍጆታቸው እንዲከፍሉ የሚደረግ አሠራር ቢዘረጋም፣ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግን አባላቱ መክፈል እንዳቆሙ ተገልጿል፡፡ በዚህም የተነሳ ኤጀንሲው ግማሽ ሚሊዮን ብር ውዝፍ ሒሳቡን እንዲከፍል በውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣኑ መጠየቁን፣ የኤጀንሲው የቅርንጫፍ 3 ኃላፊ ወ/ሮ አረግዋ ዓባይነህ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸዋል፡፡

‹‹ከቆጣሪ ንባብ ጋር የተያያዘ ችግር አለ የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ነገር ግን ያለው ችግር የቆጣሪ ንባብ ሳይሆን የክፍያ ችግር ነው፤›› በማለት ከቋሚ ኮሚቴ ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሰጡት ወ/ሮ አረግዋ፣ የምክር ቤት አባላት ለሚጠቀሙበት ክፍያ መፈጸም እንደነበረባቸው ገልጸዋል፡፡ ቀደም ብለው የነበሩ የምክር ቤት አባላት ሳይከፍሉ የፓርላማው ዘመን ስለተጠናቀቀ፣ በጉዳዩ ላይ ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ቀደም ብሎ ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ ውዝፍ ሒሳቡን ለመክፈል ስምምነት ተደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ያለመተማመን በመከሰቱና ውዝፍ እየተጠራቀመ መምጣቱን አክለዋል፡፡

ችግሩ የተከሰተው ቀደም ሲል የነበረው አሠራር በመቀየሩ መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ አረግዋ፣ ቀድሞ የነበረው አሠራር ነዋሪዎች እንደያዙዋቸው የመኖሪያ ቤቶች የመኝታ ክፍሎች ብዛት ይከፍሉ ነበር ብለዋል፡፡ ክፍያውም ለስቱዲዮ 15 ብር፣ ለሁለት መኝታ 25 ብር፣ ለሦስት መኝታ 30 ብር ያህል ለረጅም ዓመታት ይከፍል እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ከቀድሞ አሠራር መቀየር በኋላ ግን ኤጀንሲው ከቤቶቹ ኪራይ ከሚሰበሰበው በላይ ለውኃ ፍጆታ ከፍተኛ ወጪ እያስወጣው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህንኑ የወ/ሮ አረግዋን ሐሳብ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙደር ሰማን በማጠናከር፣ ‹‹ዛሬ መንግሥት ለአርሶ አደሮች እንኳ ያደርገው የነበረውን የማዳበሪያ ድጎማ ባቆመበት ወቅት በከተማ የአፓርትመንት ቤቶች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ያውም ከ200 ብርና 300 ብር ከፍ ሲልም 700 ብር በሚሆን የኪራይ ዋጋ ከመደበኛው ገበያ ከ300 እና 400 በመቶ ባነሰ ዝቅተኛ ዋጋ እያከራየን፣ ውኃ መደጎም አለበት ወይ የሚለው መታየት አለበት፤›› ብለዋል፡፡

ለነዋሪዎቹ (ለምክር ቤት አባላቱ) የውኃ ፍጆታን መደጎሙ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በተሰጠ ትዕዛዝ መሆኑን ያስረዱት አቶ ሙደር፣ መንግሥት ግለሰቦች ለተገለገሉበት ፍጆታ መክፈል እንደማይገባው እምነታቸው መሆኑን አክለው በመግለጽ፣ ‹‹አንድ ላይ ሆነን ተወያይተን ለማቆም ብንነጋገርበት ይበጃል፤›› ሲሉ ለቋሚ ኮሚቴው ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ ‹‹ወጪው ተሰልቶ ለህዳሴው ግድብ አስተዋጽኦ ብናደርገው አይሻልም?›› በማለት የጠየቁት ምክትል ዳይሬክተሩ፣ ‹‹ቋሚ ኮሚቴው በዚህ ጉዳይ ሊያግዘን ይገባል፤›› በማለትም አክለዋል፡፡

ነገር ግን የቤቶቹ ነዋሪ የሆኑና የቋሚ ኮሚቴው አባላት ያለባቸውን የውኃ ውዝፍ ለመክፈል ፈቃደኛ አይደሉም መባላቸውን አስተባብለዋል፡፡ ይልቁንም ችግሩ ከቆጣሪ ንባብ ጋር የሚያያዝና የኤጀንሲው የተዝረከረከ አሠራር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹እንደ አንድ ደንበኛ ስንመለከተው ችግሩ የተከሰተው በቤቶች ኤጀንሲ ወይም በሚመለከተው አካል ትክክለኛ መረጃ ካለመያዝ መሆኑ በደንብ ሊሰመርበት ይገባል፤›› በማለት የተናገሩት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል ናቸው፡፡

እንደ ግለሰብ ሆነ እንደ ምክር ቤት አባልነታቸው ግለሰብ ለተጠቀመበት ፍጆታ መንግሥት መክፈል ይገባዋል ብለው እንደማያምኑ አስረድተዋል፡፡ አባላት ሊከፍሉ ፈቃደኛ አይደሉም መባሉን ግን ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኤጀንሲው የተጠየቀበት ውዝፍ የፓርላማ አባላት ስለማይከፍሉ አይደለም፡፡ ቀደም ብለው ይኖሩ የነበሩ የምክር ቤት አባላትም ቢሆኑ በነበረው አሠራር መሠረት እንደየመኝታ ቤቶቻቸው ብዛት ይከፍሉ እንደነበር ነው የምናውቀው፡፡ ነገር ግን ከቆጣሪ ንባብ ጋር ተያይዞ ልዩነት እየተፈጠረ ሲመጣ በወቅቱ ቆም ብሎ ማሰብ ነበረበት፤›› ሲሉ የኤጀንሲው የአሠራር ግድፈት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

‹‹ለምሳሌ ይህን መጥቀስ ካለብኝ እኔ ቤት የምጠቀምበት የቆጠረው ቁጥርና ክፍያ እንድከፍልበት የተሰጠኝ የቆጣሪው ቁጥር የማይገናኝበት ጊዜ አለ፡፡ ይህንን በመሳሰሉ ምክንያቶች የማን ቆጣሪ የቆጠረውን ሒሳብ ነው እኔ የምከፍለው የሚል ጥያቄ በእኛ በአባላቱ መካከል ይነሳል፤›› በማለት የተከራከሩት ወ/ሮ የሺመቤት፣ በወር እስከ 370 ብር ድረስ የሚጠየቅ ነዋሪ ቢስተዋልም ያን ያህል የውኃ ፍጆታ ሒሳብ በአንድ ግለሰብ ላይ ሊመጣበት ይችላል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

ይልቁንም በተሳሳተ መረጃ ግለሰቦች ለተጠቀሙበት ሒሳብ መንግሥት ከፍሎ ከሆነ ወደኋላ ያሉ ችግሮችን በማጥራትና በመለየት፣ ለወደፊቱ ከነዋሪዎች ወርኃዊ ሒሳብ ጋር በማስላት መልሰው የሚከፍሉበትንና ወደ መንግሥት ካዝና የሚመለስበት መንገድ መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ወ/ሮ አዳነች ባዕናም የተባሉ ሌላ የምክር ቤት አባል እንዲሁ መንግሥት የግለሰቦች ፍጆታ መሸፈን እንደሌለበት እምነታቸው መሆኑን ጠቁመው፣ ‹‹ችግሩን ወደ ሌላ አካል ከማስተላለፍ ይልቅ መጀመሪያ የራሳችንን ችግር ብናየው፤›› በማለት ኤጀንሲው የምክር ቤት አባላት አልከፈሉም ከማለት ራሱን ሊፈትሽ ይገባው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ ግለሰቦች የተጠቀሙበትን የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ኤጀንሲው ሊከፍል አይገባውም በሚል እምነት ቀደም ብሎ በአባላቱ መጠየቁን ለማስረዳት የሞከሩት የምክር ቤት አባሏ፣ ‹‹አሁንም ቢሆን መንግሥት የግለሰቦችን ዕዳ ሊከፍል አይገባውም፡፡ ኤጀንሲው ያለበትን የመረጃ ክፍተት በማጥራት ችግሩን ሊያስተካክል ይገባል፤›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸው፣ ኤጀንሲውና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አለመቀናጀት ሌላኛው ችግር ነው ብለዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ ከመረጃ ክፍተት ጋር በተያያዘ የተነሳላቸውን ጥያቄ በተመለከተ ሲመልሱ ሙሉ በሒደት እንደሚያስተካክሉ ገልጸዋል፡፡ አሁን ተቋሙ አለበት የተባለውን ውዝፍ ሒሳብ እንደሚከፍል የጠቆሙት አቶ ሀብታሙ፣ ከተገለጸው የነዋሪዎች ውዝፍ ሒሳብ በተጨማሪ ለበርካታ ዓመታት የኦዲት ሒሳባቸው ያልተዘጋ ውዝፍ ሒሳቦች እንዳሉባቸው ጠቁመዋል፡፡ ለአብነት ያህል ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ ያልተሰበሰበ ሒሳብ መኖሩን ጭምር አመልክተዋል፡፡ ይህንንም ሲገልጹ በጠረጴዛቸው ላይ ከ20 ሴንቲ ሜትር የማያንስ መጠን ያለው የውዝፍ ሒሳብ ሰነድ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም በልማት ምክንያት እየፈረሱ ላሉ ቤቶች ተገቢውን ካሳ እየተከፈለ አለመሆኑን፣ ቤቶች ከመፍረሳቸው በፊት ተገቢው የመረጃ ልውውጥ እየደረሳቸው እንዳልሆነ በቋሚ ኮሚቴው ውይይት ወቅት አስረድተዋል፡፡ በምሳሌ ሲያስረዱም በቅርቡ ከፈረሱት የመንግሥት ቤቶች አሥር ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ቢታቀድም፣ መሰብሰብ የተቻለው ግን 1.6 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በልማቱ ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች መቼ እንደሚፈርሱ ቀድሞ መረጃ ስለማይሰጠው፣ ከፈረሱ በኋላም ስለፈረሱት ቤቶች መረጃ ለመሰብሰብ መቸገራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ከዚህም በከፋ ሁኔታ ለአንዳንድ ቤቶች ተከፍሏል ስለሚባለው የካሳ ክፍያ ባንክ የገባበትን ሰነድ እንኳ ማግኘት አለመቻሉንም ገልጸዋል፡፡    

 

Standard (Image)

ዶ/ር መረራ ጉዲና ለሦስተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው

$
0
0

በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ፣ ፖሊስ ለሦስተኛ ጊዜ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡

የመድረክ የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ላይ፣ ብዙ ምርመራዎችን ማድረጉን ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ፖሊስ አስረድቷል፡፡ ነገር ግን ቀሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን ገልጾ፣ ተጨማሪ 28 ቀናት እንዲቀፈድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

የዶ/ር መረራ ጠበቆች ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመቃወም፣ ደንበኛቸው ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ የተጠየቀውን የዋስትና መብት በማለፍ ፖሊስ የጠየቀውን የ28 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ ለየካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 መሠረት ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አንድ ዕድል ይቀረዋል፡፡ 

Standard (Image)

በማምረት ሙከራ ላይ መሆናቸውን የሚገልጹ የማዕድን ኩባንያዎች ላይ ክትትል እንዲደረግ ፓርላማው አሳሰበ

$
0
0

- በሚድሮክ ወርቅ ልማት ላይ ጥቆማ ቀርቧል

በማዕድን ዘርፍ የተሠማሩ ኩባንያዎች የማምረት ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ የማምረት ሙከራ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ለዓመታት እያጭበረበሩ እንደሚቆዩ እንደተደረሰበት በመግለጽ፣ ክትትል እንዲደረግ የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ረቡዕ ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. የማዕድን፣ ተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ሚኒስቴርን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ባቀረበበት ወቅት ነው ይኼንን ማሳሰቢያ የሰጠው፡፡  

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ጀምበርነሽ ለንፉ ለሚኒስቴሩ አመራሮች ማሳሰቢያውን በሰጡበት ወቅት፣ ቋሚ ኮሚቴው የማዕድን ዘርፉን በአካል በየቦታው በመዘዋወር እንደጎበኘ አስታውሰዋል፡፡

‹‹ሕገወጥ የማዕድን ዝውውር እናንተ ከምትሉትና እኛም ከምንገምተው በላይ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የማዕድን ፈቃድ ወስደው ለዓመታት የመንግሥትን ጥቅም የሚያሳጡ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ከዚህ ቀደም ወደ ሻኪሶ አቅንቶ ሻኪሮ በሚባል አካባቢ ያለውን የወርቅ ልማት ለመመልከት እንደሞከረ የተናገሩት ወ/ሮ ጀምበርነሽ፣ በዚህ ሥፍራ ያለው የሚድሮክ ወርቅ ልማት ገና በሙከራ ላይ ቢሆንም እውነቱ ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ ለሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳና ለባልደረቦቻቸው አሳስበዋል፡፡

በወርቅ ልማት ክልል ውስጥ ገብተው እንዳዩ የተናገሩት ምክትል ሰብሳቢዋ ‹‹እዚያ ያለ ባለሙያ ጭምር የገለጸው ከ21 ካራት በላይ የሆነ ጥራት ያለው ወርቅ እየተመረተ ከሻኪሮ ወደ ዋናው ሚድሮክ እየመጣ ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ሚድሮክ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሙከራ ላይ መሆኑን ቢገልጽም፣ በተጨባጭ ግን እየተመረተ ስለመሆኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመከታተል የመንግሥትን ጥቅም እንዲያስከብር አሳስበዋል፡፡

በሌሎች ማዕድናት ላይ ሙከራ ላይ መሆናቸውን እየገለጹ ለዓመታት የሚቆዩትን ኩባንያዎች መመርመር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ በአጠቃላይ የማዕድን ዘርፉ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ በመሆኑ በጥልቀት ሊመረመር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በተለያዩ የማዕድን ልማት አካባቢዎች ቱሪስት መስለው የሚንቀሳቀሱ የውጭ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ የከበሩ ማዕድናትን እያወጡ መሆኑን፣ በተለይም ኦፓል የተሰኘውን ማዕድን የራሳቸው አድርገው በድረ ገጽ ጭምር የሚለቁ መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የግል ባለሀብቶች ከውጭ ዜጎች ጋር አቅደው የማጭበርበር ተግባር የሚፈጽሙ መኖራቸውን ኮሚቴው እንደደረሰበት በመጠቆም ዕርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ መልስ የሰጡት ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቀሳ የተሰጡዋቸውን ማሳሰቢያዎች ተቀብለው እንደሚመረምሩ ተናግረዋል፡፡ ዘርፉ ግን ሙሉ ለሙሉ ለሙስና ተጋላጭ መሆኑን፣ ከፍተኛ ሀብት የሚያንቀሳቅሱ የውጭ ኩባንያዎች በቀላሉ ሁሉንም በገንዘባቸው እንደሚጠመዝዙ አክለዋል፡፡ በሚድሮክ ወርቅ ላይ የቀረበውን ጥቆማ አስመልክቶ ሪፖርተር ከሚድሮክ ወርቅ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡   

 

 

 

Standard (Image)

በድንበር ማካለል ችግር ከአዲስ አበባ መሬት የወሰዱ ባለሀብቶችን ኦሮሚያ ክልል እንዲያስተዳድራቸው ተወሰነ

$
0
0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን መካከል ለዓመታት በዘለቀው የድንበር ማካለል ችግር ሲጉላሉ የቆዩና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት የወሰዱ 38 ኢንቨስተሮች በኦሮሚያ ክልል እንዲተዳደሩ ተወሰነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚዋሰንባቸው በተለይ በሰበታና በገላን ከተሞች አቅራቢያ፣ ለኢንቨስተሮችና ለመንግሥት ተቋማት ለልማት የሚሆን መሬት በተለያዩ ጊዜዎች ሰጥቷል፡፡

ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለልማት ያስተላለፋቸው በርካታ ቦታዎች፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ክልል ነው በሚል ተቃውሞ ተነስቷል፡፡ በሁለቱ አስተዳደራዊ አካላት መካከል የተፈጠረው የቦታ ይገባኛል ውዝግብ፣ በወቅቱና በአግባቡ ባለመፈታቱ በርካታ ባለሀብቶች ሲጉላሉ መቆየታቸው ይነገራል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት አዲስ አበባ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ደብዳቤዎችን የተለዋወጡ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ጥር 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ለከተማው የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ፣ የ38 ባለሀብቶች ፋይል ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲላክ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትና የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ እሸቱ ደሴ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሐምሌ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤ፣ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ አቅራቢያ ለተለያዩ ባለሀብቶች የኢንዱስትሪ መሬት መስጠቱን አስታውሰዋል፡፡ አስተዳደሩ የሰጣቸው ቦታዎች ከሰበታ አስተዳደር መሬት ጋር የተደራረቡ በመሆናቸው፣ የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ የመለየትና የማካለል ሥራ   እስኪጠናቀቅ ድረስ ባለሀብቶች መጉላላት ስለሌለባቸው፣ ሙሉ ፋይላቸው ለኦሮሚያ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ እንዲላክ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

‹‹የክልሉ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት የተፈቀደላቸው ባለሀብቶች በዚህ በተፈጠረው ችግር ምክንያት መጉላላታቸው ተገቢ ባለመሆኑ ሙሉ በሙሉ ፋይላቸውን ተረክቦ ለማስተናገድ ተወስኗል፤›› ሲሉ አቶ እሸቱ ለከንቲባ ድሪባ በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የኦሮሚያ ክልል ጥያቄን ሙሉ ለሙሉ ተቀብሏል፡፡ አቶ አሰግድ ከኦሮሚያ ክልል የተጻፈውን ደብዳቤ ዋቢ በማድረግ ለከተማው መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ፣ ድንበር የማካለሉ ጉዳይ ወደፊት የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እስኪፈታ ድረስ ባለሀብቶቹ ወደ ልማት መግባት እንዲችሉ የባለሀብቶቹን ፋይል ለኦሮሚያ ክልል እንዲላክ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ወሰን ማካለል ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ቦታዎቹ ለልማት በሚፈለጉበት ወቅት ይገባኛል ጥያቄ እየተነሳ፣ በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ መስተጓጎል ይፈጠራል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት ይህንን ችግር ለመፍታት በርካታ ንግግሮች ቢካሄዱም፣ አሁንም የወሰን ጉዳይ ጎልቶ የሚነሳና ወደ ሥራ ለመግባት ቦታ የወሰዱ ባለሀብቶችም እያጉላላ ነው፡፡

ባለሀብቶቹ ለጊዜው በኦሮሚያ ክልል እንዲተዳደሩ የተወሰነ ቢሆንም፣ ለወደፊቱ ችግሩን በኮሚቴ ለመፍታት መታቀዱ ታውቋል፡፡

Standard (Image)

ስሙን የቀየረው ፒቲኤ ባንክ ለአገር ውስጥ ኩባንያዎች 60 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለቀቀ

$
0
0

- ለአፍሪካቀንድ አገሮች አገልግሎት የሚሰጠውን ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ይከፍታል

ከተመሠረተ 30ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የንግድና የልማት ባንክ (ፒቲኤ ባንክ) ስያሜውን በመቀየር ወደ ንግድና ልማት ባንክነት በተቀየረበት ሰሞን፣ ለሦስት የአገር ውስጥ ኩባንያዎች 60 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማፅደቁን አስታወቀ፡፡

አዲሱን ስያሜውን በአዲስ አበባ ይፋ ባደረገበት ወቅት የባንኩ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ይልማ ታደሰ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ እንይ ጄነራል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ፣ እንዲሁም ጋቴፕሮ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኩባንያ እያንዳንዳቸው የ20 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ከሦስቱ ኩባንያዎች በተጨማሪ ሌሎችም በድርድር ሒደት ላይ የሚገኙ እንዳሉና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉም ጠቁመዋል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት ዓለም አቀፍ ብራንድ ሆቴል ለመክፈት በካሊብራ አማካሪ ኩባንያ አማካይነት ከፈረንሣዩ አኮር ግሩፕ ጋር ስምምነት ያደረገው እንይ ኩባንያ፣ አኮር ከሚስተዳድራቸው ውስጥ ፑልማን የተባለውን ብራንድ ሆቴል በኢትዮጵያ ለመክፈት የ20 ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያስፈልገውና ከፈረንሣይ አበዳሪ ተቋማት ብድሩን ለማግኘት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ ተቋም (ኮሜሳ) ባንክ ከሆነው የንግድና የልማት ባንክ ብድሩን ሊያገኝ በመቻሉ፣ የሆቴል ፕሮጀክቱን በቅርቡ ዕውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ጋቴፕሮ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኩባንያም የ20 ሚሊዮን ዶላር ብድር የፀደቀለት ለሚገነባው የብረታ ብረት ፋብሪካ እንደሆነ ታውቋል፡፡  

አቶ አድማሱ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች የሚውል ብድር ለመልቀቅ ባንካቸው ዝግጁ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ እስከ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ብድር ለመስጠት ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ 

የአሁኑ የንግድና የኢንቨስትመንት ባንክ ከዚህ ቀደም ለሐበሻ ሲሚንቶ የ50 ሚሊዮን ዶላር ብድር መልቀቁን አቶ አድማሱ አስታውሰዋል፡፡ ከሐበሻ ሲሚንቶ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድም 40 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘቱ አይዘነጋም፡፡ ከእነዚህ ተቋማት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከ200 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ብድር እንደሚለቀቅለት መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

ባንኩ ለኢትዮጵያ ከሚሰጣቸው የፋይናንስ አገልግሎቶች በተጨማሪ በጎረቤት አገሮች ማለትም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለሚገኙ አገሮች ተደራሽ የሚሆን የቀጣናውን ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ለመክፈት እንዲችል፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ከወራት በፊት ያደረገውን ስምምነት ወደ ተግባር በመለወጥ በኦሎምፒያ አካባቢ ጽሕፈት ቤቱን ለመከፈት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን አቶ አድማሱ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሠረት የሰው ኃይል ማሟላትን ጨምሮ፣ ከውጭ የሚገቡ ልዩ ልዩ መገልገያዎች እንዲመጡለት ማዘዙን ጠቁመዋል፡፡

በቡሩንዲዋ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ የነበረውን ጽሕፈት ቤት በአገሪቱ በተከሰተው ብጥብጥ ምክንያት ለመዝጋት መገደዱ ታውቋል፡፡ የቡጁምቡራ ጽሕፈት ቤቱን ወደ ኬንያ ያዛወረው የንግድና የልማት ባንኩ፣ በታሪክ በአንድ ጊዜ ሲፈቅድ የመጀመርያው የሆውን የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኬንያ አፅድቋል፡፡ የባንኩን ስያሜ መቀየር ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል በየጊዜው እያደገና ለውጥ እያሳየ ከመምጣቱ ጋር እንደሚያያዝ፣ ከዚህም ባሻገር የኮሜሳ አባል ያልሆኑ አገሮችንም ለማካተት ታስቦ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ አድማሱ በዚህም እንደ ሞዛምቢክ፣ ደቡብ ሱዳንና ታንዛንያ ያሉ አገሮች በቅርቡ ወደ አባልነት መቀላቀላቸውን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው አባል አገሮችን ጨምሮ እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ያሉ ተቋማትን በባለድርሻነት ያቀፈው ይህ ባንክ፣ በአቶ አድማሱ መመራት ከጀመረ ወዲህ የነበረውን አንድ ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅም በ300 ፐርሰንት በማሳደግ አራት ቢሊዮን ዶላር ማድረስ ችሏል፡፡ ለዚህ ለውጥ ትልቁን ሚና የተጫወቱት አቶ አድማሱ በኮሜሳ ዋና ጸሐፊ ሲንዲሶ ንዴማ ንግዌንያ ተሞካሽተዋል፡፡

የባንኩ የዳይሬክትሮች ቦርድ አማካሪ እንዲሆኑ የተመረጡት የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዘዲንዳት ሩፒያህ ባንዳም ስለ አቶ አድማሱ ብቃት ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ባንዳ በወጣትነት ዘመናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአራት ኪሎ ካምፓስ ተማሪ እንደነበሩ አስታውሰው፣ በንግግራቸው ወቅት በአማርኛ ሰላምታ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡

አቶ አድማሱ በዓለም ትልቅ ክብርና ዝናን ካተረፉ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚና በባንክ ሙያ መስኮች ተቀብለዋል፡፡ በሐርቫርድ፣ በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፖለቲካል ሳይንስ፣ እንዲሁም በሌሎች የአውሮፓና  የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ባለቤታቸው ሱፐር ሞዴል አና ጌታነህም ታዋቂነትን ያተረፈች የሞዴል ባለሙያ ከመሆኗም በላይ፣ አፍሪካ ሞዛይክ የተባለውንና በፋሽን ኢንዱስትሪው ተቀባይነት ያተረፈውን ዓመታዊ የፋሽን ትርዒት በማዘጋጀት ሁለት አሥርት ገደማ አስቆጥራለች፡፡ ከዚህ ሙያዋ በተጨማሪ ሕፃናትን የሚረዳና የኢትዮጵያ ሕፃናት ፈንድ የተባለ ግብረ ሰናይ ተቋም በአሌልቱ አካባቢ በመመሥረት ከባለቤቷ ከአቶ አድማሱ ጋር እያንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡ 

 

 

Standard (Image)

ንግድ ሚኒስቴር የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት ላይ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ

$
0
0

-  ለአባልነት የሚደረገው ድርድር ከ14 ዓመታት በላይ ፈጅቶም ጅምር ሒደት ላይ ይገኛል

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት በአምስት ዓመታት ውስጥ ለማጠቃለል እየሠራች እንደምትገኝና በአባልነት ድርድር ሒደቱ የተጠየቁ መሥፍርቶችን ለማሟላት የሚያስችሉ ጥናቶችና ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት ላላደጉ አገሮች ድጋፍ ለመስጠት ያስችላል ያለውን የተቀናጀ የንግድ ማሻሻያ ማዕቀፍ ፕሮግራም ዘርግቶ በሚሰጠው ድጋፍ ተጠቃሚ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ለአምስት ቀናት የሚቆየውን ዓውደ ጥናት በማስተናገድ ላይ ትገኛለች፡፡ የተቀናጀ የንግድ ማሻሻያ ማዕቀፍ (Enhanced Integrated Framework) የተባለና በማደግ ላይ ለሚገኙ አገሮች ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ተመሥርቶ፣ ለአገሮቹ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

ተቋሙ ለኢትዮጵያ የሚሰጣቸውን ድጋፎችና ሌሎች አገልግሎቶች በንግድ ሚኒስቴር በኩል በተጠባባቂነት የሚያስተባብሩት አቶ ደምለው መኮንን እንዳብራሩት ተቋሙ የአቅም ግንባታ፣ የተቋማዊና የሰው ኃይል አደረጃጀቶች ላይ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በየዓመቱም እስከ 900 ሺሕ ዶላር የሚጠጋ የፋይናንስ ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ በሚቀርቡለት ትልልቅ ሐሳቦች መነሻነትም እስከ ሦስት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ድጋፍ እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡

ይህ ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአራት በላይ በማደግ ላይ የሚገኙ ደሃ አገሮች ወደ ዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት የሚገቡበትና በዓለም ዓቀፍ የንግድ መድረኮች ተጠቃሚ መሆን የሚችሉባቸውን ዕድሎች ለመፍጠር ታስቦ የሚደረግ መሆኑን ከአቶ ደምለው ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተለይም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች እሴት ታክሎባቸው የሚወጡና ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ እንዲሆኑ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ አባል ለመሆን የሚያስችላትን የድርድር ሒደት ከጀመረች ከ14 ዓመታት ቆይታ በኋላም፣ አሁንም ዝግጅት እያደረገች እንደምትገኝ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት የሸቀጦች ታሪፍና መሰል መጠይቆችን የሚመለከተውን የድርድር ሒደት ማካሄዷን አቶ ደምለው አስረድተዋል፡፡ በዚህ ሒደት ኢትዮጵያ የሌሎች አገሮችን ሸቀጦች የምታገበያይበትን የታሪፍ ምጣኔ ማሳወቋ አይዘነጋም፡፡ ይህ የድርድር ሒደት ከተጀመረ ዓመታትን አስቆጥሮም አሁንም ድረስ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለመሻገር ገና ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተብራርቷል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት አባላት ኢትዮጵያ የታሪፍና መሰል ጉዳዮች ላይ ያቀረበቻቸውን ትልቅ ሐሳቦች በማስመልከት፣ የድርጅቱ አባል አገሮች ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚደረጉ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን በአገልግሎት መስኮች ኢትዮጵያ ለድርድር የምታቀርባቸውን ሐሳቦች ለተደራዳሪ አገሮች የምትልክበት ሒደት እንደተጓተተ ቢታወቅም፣ በዚህም መስክ በሚኒስትሮች የሚመራ ምክር ቤት ተቋቁሞ እየሠራ እንደሚገኝ ከመገለጹ በቀር ሒደቱን የሚያብራራ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ለመረዳት እንደተቻለው መንግሥት ስለጉዳዩ በዝግ እየሠራ ነው፡፡ ለዓለም ንግድ ድርጅትም ቢሆን በአገልግሎት መስክ ስላለው አቋም ምላሽ እየሰጠ እንዳልሆነ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ የተያዘው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት፣ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መጨረሻ ዕውን ይሆናል ተብሎ መጠቀሱ የሚታወቅ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የሚመራው አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ከፈረሙ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ብትሆንም፣ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ግን በማቅማማት ላይ ትገኛለች፡፡ ለዚህ በዋነኝነት የሚጠቀሰው አገሪቱ የሌሎች አገሮችን ምርቶች ለመወዳደር የሚያስችሏትና ወደ ውጭ ሊላኩ የሚችሉ ምርቶች እንደ ልብ የማታመርት መሆኑ የፈጠረው ሥጋት ነው፡፡  

በዓለም ንግድ ድርጅት በኩል ለአገሮች የንግድ ዘርፍ መጎልበት ድጋፍ የሚሰጠው ማዕቀፍ ከተመሠረተ በኋላ፣ ኢትዮጵያ የማዕቀፉ ተጠቃሚ መሆን ከጀመረች ሁለተኛ ዓመት አስቆጥራለች፡፡ ስድስት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ተቀናጅተው በሚሰጡት የንግድ ማጎልበት ድጋፍ እንቅስቃሴ ላይ 24 የበለፀጉ  አገሮች የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት የተቋሙን ሥራዎች እንደሚያግዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

 

Standard (Image)

ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያገናኝ መንገድ እየተገነባ ነው

$
0
0

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳንን በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር ከተያዙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የመንገድ አውታር ግንባታ፣ በኢትዮጵያ በኩል እየተካሄደ ነው፡፡ ደቡብ ሱዳንም ይኼንን ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር መክራለች፡፡

ኢትዮጵያ ከሚዛን ዲማ፣ ከዲማ ራድ ድረስ የመንገድ አውታር ግንባታ በማካሄድ ላይ ትገኛለች፡፡  ከሚዛን ዲማ ድረስ ያለውን 91 ኪሎ ሜትር መንገድ የቻይና ኩባንያ የሆነው ኤምሲሲ፣ ከዲማ የድንበር ከተማ እስከሆነው ራድ ድረስ ያለውን 62 ኪሎ ሜትር መንገድ የኢትዮጵያ መንገዶች ኮርፖሬሽን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እነዚህ ፕሮጀክቶች ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ በሚቀጥለው ዓመት ይጠናቀቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ሳምሶን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከራድ እስከ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ድረስ ያለውን መንገድ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ የሚገኙት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሁለቱ አገሮች ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተነጋግረዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የኢትዮጵያንና የደቡብ ሱዳንን ግንኙነት ለማጠናከር አገሮቹ የመሠረተ ልማት ግንባታ በተለይም የመንገድ፣ የባቡርና የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታዎችን በጋራ ለማካሄድ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አላቸው ተብለው ከሚታመኑ ኮሪደሮችና ጎረቤት አገሮች ጋር በመንገድና በባቡር በመተሳሰር ላይ ትገኛለች፡፡ ለመተሳሰርም የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተነድፈው እየተሠሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ኢትዮጵያ (ጋምቤላ) በማስገባት የነዳጅ ማጣሪያ የማቋቋም ዕቅድ ተይዟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ባቀረቡላቸው ግብዣ መሠረት ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በቅርቡ አዲስ አበባ ተመልሰው የሚመጡ ሲሆን፣ በዚያን ወቅት ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የተለያዩ ስምምነቶችን ይፈርማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡    

Standard (Image)

ለውጭ ገበያ ይቀርባል የተባለውን ያህል ቡና አልቀረበም

$
0
0

- አንዱ ምክንያት በላኪዎች ላይ የተወሰደው ዕርምጃ ነው ተብሏል

ከቡና፣ ቅመማ ቅመምና ከሻይ ቅጠል ምርቶች በግማሽ በጀት ዓመት ይገኛል ተብሎ የታቀደውን ያህል አለመቅረቡ ታወቀ፡፡ ለዚህም በቅርቡ በቡና ላኪዎች ላይ የተወሰደው ዕርምጃ ዋናውን ድርሻ እንደሚይዝ ተጠቁሟል፡፡ ከቡናና ሻይ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ በ2009 በጀት ዓመት የመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት 107,271 ቶን ቡና፣ ቅመማ ቅመምና የሻይ ቅጠል ምርቶችን ለውጭ ገበያ አቅርቦ 401.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የተገኘው ግን 321.2 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡

ከሦስቱም ምርቶች ከታቀደው ውስጥ መላክ የተቻለው 89,574 ቶን በመሆኑ፣ በዕቅዱና በክንውኑ መካከል ከ27 ሺሕ ቶን በላይ ልዩነት ታይቷል፡፡

በተለይ በግማሽ በጀት ዓመቱ ለውጭ ገበያ የቀረበው የቡና መጠን ካለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ያነሰ ሲሆን፣ በምርት ዘመኑ ግን የአገሪቱ የቡና ምርት በ26 በመቶ ጨምሯል፡፡

እንደ ባለሥልጣኑ መረጃ በግማሽ በጀት ዓመቱ 98,561 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ይቀርባል ተብሎ ማቅረብ የተቻለው 85,425 ቶን ነው፡፡ ከገቢ አንፃርም ቡና ያስገኛል ተብሎ ታሳቢ የተደረገው 385 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የተገኘው 315.7 ሚሊዮን ዶላር በመሆኑ ገቢው ከዕቅዱ ወደ 19 በመቶ ሊያንስ ችሏል፡፡

በ2008 ግማሽ የበጀት ዓመት ግን ለውጭ ገበያ የቀረበው ቡና 87,785 ቶን ሲሆን፣ ይኼም በ2009 በጀት ዓመት ግማሽ በጀት ዓመት ከተላከው ጋር ሲነፃፀር በ2,332 ቶን ወይም የ2.7 በመቶ የቀነሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሆኖም ከገቢ አንፃር የተገኘው የውጭ ምንዛሪ የዘንድሮው ግማሽ ዓመት በ2.8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ባለፉት ጥቂት ወራት የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በመሻሻሉ ነው፡፡

ቡና የዕቅዱን ያህል ለውጭ ገበያ ላለመቅረቡ የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡ ባለፉት ዓመታት በሕገወጥ መንገድ የኤክስፖርት ቡና ምርት ከገበያ ገዝተው መላክ ባልቻሉ ላኪዎች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ ከመወሰዱ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የባለሥልጣኑ የስድስት ወራት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በምርት ገበያው ያላቸውን ወንበር በመጠቀም ምርት የገዙላቸው አንዳንድ የምርት ገበያው አገናኝ አባላት በሆኑ ላኪዎች ላይ የተወሰደው የዕግድ ዕርምጃ የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁመው የባለሥልጣኑ ሪፖርት፣ ቡና ላኪዎች በበጀት ዓመቱ ሦስት ወራት  (ከሐምሌ እስከ መስከረም) ቀደም ብሎ የዓለም ቡና ዋጋ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ላይ ኮንትራት በመፈጸማቸው ከአገር ውስጥ ዋጋ ጋር መናበብና በግዥ መሟላት አለመቻሉ ለአፈጻጸሙ መቀነስ ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡

ባለፈው ዓመት በተከሰተው የኤልኒኖ የአየር ጠባይ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች በጥራት ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ በማሳደሩ፣ የተወሰኑ ላኪዎች የገቡትን ኮንትራት ለማሟላት በቂ ጥረት ያለማድረግ፣ የውጭ ቡና ገዥ ኩባንያዎች አዲሱን ምርት የመጠበቅ አዝማሚያ ማሳየታቸውም ተጨማሪ ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡

በተለይ የሻይ ቅጠልና የቅምማ ቅመም ምርቶች አቅርቦት ከተጠበቀው ውጤት በታች ተመዝግቦበታል፡፡

በሪፖርቱ እንደተገለጸው፣ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ለውጭ ገበያ ይቀርባል ተብሎ የታቀደው 7,192 ቶን ቅመማ ቅመም ምርት ቢሆንም፣ የተላከው 3,200 ቶን ብቻ ነው፡፡ ይኽም የዕቅዱን 44 በመቶ ብቻ ማሳካት የተቻለ መሆኑን  ያሳያል፡፡ በገቢም ረገድ ከቅመማ ቅመም ምርቶች የወጪ ንግድ ይገኛል የተባለው ገቢ ከግማሽ በላይ እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡ የታቀደውን ያህል ቅመማ ቅመም ቢላክ ኖሮ 13.5 ሚሊዮን ዶላር የሚገኝ ቢሆንም፣ በስድስት ወራት መገኘት የቻለው ግን 5.7 ሚሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዱ 42.5 በመቶው ብቻ ነው፡፡

በተመሳሳይ የሻይ ቅጠል ምርት የወጪ ንግድም በዕቅዱና በክንውኑ መካከል ልዩነት ታይቶበታል፡፡ በባለሥልጣኑ መረጃ መሠረት በመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት  1,517 ቶን ሻይ ቅጠል ለውጭ ገበያ አቅርቦ 2.7 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ቢታቀድም፣ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለው 948 ቶን ብቻ ነው፡፡ የተገኘው ገቢም 1.7 ሚሊዮን ብር ብቻ በመሆኑ የገቢ አፈጻጸሙ 64 በመቶ ሊሆን ችሏል፡፡

 

Standard (Image)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ጋር እየመከረ ነው

$
0
0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለልማት ሲባል በተነሱ ነገር ግን ለችግር የተዳረጉ አርሶ አደሮችን በድጋሚ ለማቋቋም በመሠረተው አዲስ ፕሮጀክት ጉዳይ ላይ፣ ከአርሶ አደሮች ጋር የመጀመሪያ ዙር ውይይት አካሄደ፡፡

ማክሰኞ ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በአምስት ቦታዎች ላይ 2,000 ከሚጠጉ ተነሺ አርሶ አደሮች ጋር ውይይት በማድረግ 35 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‹‹የተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት›› በሚባል ስያሜ አዲሱን ፕሮጀክት ካቋቋመ በኋላ በተከናወኑ ጉዳዮች ላይ ለአርሶ አደሮቹ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ተነሺ አርሶ አደሮቹ በወቅቱ እንደገለጹት፣ በቂ ካሳና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ሲወርድ ሲዋረድ ከኖሩበትና ብቸኛ ሙያቸው ከሆነው ግብርና ሥራ እንዲራራቁ መደረጉ ለከፋ ችግር ዳርጓቸዋል፡፡

ተነሺ አርሶ አደሮቹ መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን መልሶ ለማቋቋም ማቀዱ መልካም መሆኑን ገልጸው፣ ነገር ግን የተጀመረው ሥራ መና እንዳይቀር አሳስበዋል፡፡

አወያዮቹ መንግሥት በችግር ውስጥ ያሉትን ተነሺ አርሶ አደሮች በድጋሚ ለማቋቋም ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸውላቸዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ተነሺ አርሶ አደሮቹ ኮሚቴ እንዲመርጡ የተደረገ ሲሆን፣ ተነሺ አርሶ አደር ያሉባቸው አምስት ክፍላተ ከተሞች ሰባት፣ ሰባት ሰዎችን የኮሚቴ አባል አድርገው መርጠዋል፡፡

የተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አቡዱራዛቅ ያሲን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከአምስቱም ክፍላተ ከተሞች የተመረጡት 35 ሰዎች የራሳቸውን ስብሰባ አድርገው አምስት ሰዎችን ለቦርድ አባልነት ያቀርባሉ፡፡

እነዚህ በልማት ምክንያት ከቦታቸው የተነሱ አርሶ አደር የኮሚቴ አባላት፣ መቋቋም ያለባቸውን አርሶ አደሮች በመለየት ሒደት ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው አቶ አብዱራዛቅ ገልጸዋል፡፡

‹‹በአምስት ደረጃዎች ተከፍሎ አርሶ አደሮችን የማቋቋም ሥራ ይሠራል፡፡ ለአብነት ያህል በመጀመሪያ ምንም ገቢ የሌለው አነስተኛ ገቢ ያለውን በመለየት በአፋጣኝ ማቋቋም ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ገቢ ያለው ከሆነ ወደ ኢንቨስተር ደረጃ የማሳደግ ሥራ ይሠራል፤›› ሲሉ አቶ አብዱራዛቅ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ሥራ ከተጀመረበት ከ1990 ዓ.ም. ወዲህ ባሉ ዓመታት፣ በከተማው ዳርቻ አካባቢዎች የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ከኖሩበት ቀዬ ለልማት ተነስተዋል፡፡  

አርሶ አደሮቹ በቂ ካሳና በቂ ምትክ ቦታ ካለማግኘታቸው በተጨማሪ፣ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ደንብና መመርያ የሚፈቅዷቸውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ የሚፈቀድ ቢሆንም፣ በርካታ ወጣቶች ይህን አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለችግር የተዳረጉ አርሶ አደሮችን በድጋሚ ለማቋቋም ዕቅድ አውጥቷል፡፡ ክፍላተ ከተሞቹ ቦሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ አቃቂ ቃሊቲ የካና ኮልፌ ቀራኒዮ ናቸው፡፡  

አቶ አብዱራዛቅ እንዳሉት 2009 ዓ.ም. የዝግጅት ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን በተቻለ መጠን 20 ሺሕ አርሶ አደሮችን በድጋሚ ለማቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ 

Standard (Image)

የተመድ ዋና ጸሐፊ ዓለም ኢትዮጵያን ከድርቅ አደጋ እንዲታደግ ጥሪ አቀረቡ

$
0
0

‹‹የምናባክነው ጊዜ ሊኖር አይገባም›› የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ

አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን ድርቅ እንድትቋቋም በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ፡፡ ለአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ የመጡት ጉተሬዝ ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ስቴፈን ኦሪን ጋር በሰጡት መግለጫ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለኢትዮጵያ አጋር መሆኑን የሚያሳይበት ወሳኝ ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ይኼ ወቅት ዓለም ለኢትዮጵያ አንድነቱን የሚያሳይበት ነው፡፡ እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አጋርነትን ማሳየት የለጋሽነት ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁንም ፍትሐዊነትና የራስ ፍላጎትን ማሳያ ሊሆን ይገባዋል፤›› ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው 5.6 ሚሊዮን ዜጎች በፍጥነት ሊደረስላቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ድንበራቸውን ክፍት አድርገው በአፍሪካ አንደኛ ስደተኞችን አስተናጋጅ መሆናቸው የለጋስነታቸውን መጠን ያሳያል ያሉት ጉተሬዝ፣ ለአሥር ዓመታት የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ሆነው መሥራታቸው ይህንን ከፍተኛ የሆነ ለጋስነት እንዳሳያቸው ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር ባለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ብለው፣ ዓለም ለስደተኞች ድንበሩን በዘጋበት ጊዜ መሆኑ ደግሞ ሊታወስ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ የአሁኑ አዲሱ ድርቅ ከአየር ንብረት መለዋወጥ ጋር የተያያዘና ተከታታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአካባቢው ‹‹የመረጋጋት ምሰሶ›› ናት ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድርቁ ለተጨማሪ አለመረጋጋት፣ ማኅበራዊ ሁከት ወይም ለግጭት ማባባሻ እንዲሆን መፍቀድ የለበትም ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስደተኞችን ለመቀበል ፍላጎት በሌለበት በዚህ ጊዜ በድርቁ ምክንያት የዜጎች መፈናቀል እንዳይፈጠር ፈጣን ምላሽ መገኘት አለበት ሲሉ አክለዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽብር ሥጋት መንሠራፋቱ ብዙ አገሮችን እያስፈራ ስለሆነ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን በማገዝ የድርቁ ተፅዕኖ መቀነስ አለበት ብለዋል፡፡ ምክንያቱን ሲያስረዱ ዜጎች በድርቁ ጉዳት ሳቢያ ለስደት እንዳይዳረጉ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር በሚፈጠር የትግል አንድነት አብሮ መሥራት የሚያስፈልገው አሁን ያለውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከማሟላት ብቻ ሳይሆን፣ በልማት መስክ የሚታየውን ከፍተኛ ተግዳሮት ለመቀልበስ በሚደረገው ጥረት ለመተባበርና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ዓለም እየተጋፈጠ ያለውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ከማድረግ አንፃር ነው በማለት ጉተሬዝ አስረድተዋል፡፡

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ስቴፈን ኦሪን በበኩላቸው፣ ለሦስት ቀናት በደቡባዊ ምሥራቅ የአገሪቱ ክልሎች ባደረጉት ጉብኝት የአሁኑ ድርቅ በሰዎች ሕይወት ላይ የደቀነውን አደጋ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በዋርዴር ዞን ድርቁ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሯል ያሉት ኦሪን፣ ከመዘግየት በፊት በፍጥነት ዕርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ለ2017 በወጣው የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰነድ መሠረት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ 5.6 ሚሊዮን የድርቅ ተጎጂ ወገኖችን ለመታደግ 948 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማድረግ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

‹‹የምናባክነው ጊዜ ሊኖር አይገባም፡፡ እንስሳት እየሞቱ ነው፡፡ አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች ከእንስሳት ውኃና ግጦሽ ፍለጋ ከቀዬአቸው ርቀው እየሄዱ ነው፡፡ ሕፃናት በተለይም ሴቶች ከትምህርት ቤት እየቀሩ ወላጆቻቸውን በሥራ እያገዙ ነው፡፡ ዕርዳታ በጊዜው ካልደረሰ ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት በቅርቡ እየጨመሩ ይሄዳሉ፡፡ በዚህም ሴቶች ከጤና ጋር በተያያዘ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፤›› በማለት ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የተመድ ዋና ጸሐፊ ጉተሬዝ፣ ‹‹የአሁኑ የድርቅ ቀውስ የገጠመው የኢትዮጵያ መንግሥት ስላልተዘጋጀበት ሳይሆን፣ የድርቁ ስፋት ከአገሪቱ አቅም በላይ በመሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በቋሚነት ድርቅን የሚቋቋም ፖሊሲ ሥራ ላይ በማዋል ተፅዕኖዎችን መቋቋም የቻለች አገር ናት፡፡ አሁን ግን ያጋጠመው የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠረውና በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በመከሰቱ ነው፤›› በማለት፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለዚህች አገር አጋርነት በአንድነት ሊቆም ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  

በሌላ በኩል መንግሥት በአገሪቱ የተወሰኑ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በሰው ሕይወትና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ርብርብ እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለ5.6 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ የአንድ ቢሊዮን ብር በጀት ማፅደቁን አስታውቀዋል፡፡ 

Standard (Image)

የአራት አግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ግንባታ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊጀመር ነው

$
0
0

-  የአገር ውስጥ ምግብና መጠጥ አምራቾች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እንዲተኩ ጥሪ ቀረበ

በአራት ክልሎች የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊጀመር እንደሆነ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶችን የሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች የሚገነቡባቸው ሲሆን፣ ፓርኮቹ የሚገነቡት በአማራ ክልል ቡሬ፣ በምዕራብ ትግራይ ባከር፣ በኦሮሚያ ዝዋይ አካባቢ ቡልቡላ፣ በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ ነው፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር መብራህቱ መለስ ማክሰኞ ጥር 23 ቀን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት በቅርቡ ተካሂዶ ወደ ግንባታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እያንዳንዳቸው በ250 ሔክታር ቦታ ላይ በፓይለት ፕሮጀክት ደረጃ ተጀምሮ ወደ 1,000 ሔክታር እንደሚሰፉ ዶ/ር መብራህቱ አስረድተዋል፡፡ ፓርኮቹን በባለቤትነት የሚገነቡት በየክልሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽኖች መቋቋማቸውን ገልጸዋል፡፡ የግንባታ ወጪው በመንግሥት፣ በአገር ውስጥና በውጭ ባንኮች በሚገኝ ብድር እንደሚሸፈን ተገልጿል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ግንባታ 17 ቀጣናዎች መለየቱን፣ በፓይለት ፕሮጀክት ደረጃ የመጀመሪያዎቹ የአራቱ ፓርኮች ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡ የቀጣናዎቹ መረጣ የተካሄደው በዋናነት የጥሬ ዕቃዎች ምርት መገኛ መሠረት በማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ለአራቱም ፓይለት ፓርኮች በቅድሚያ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትና ከዓለም የምግብ ድርጅት ጋር በመተባበር ዝርዝር የአዋጭነት ጥናት አካሂዷል፡፡ በዚህ መሠረት ዝርዝር የምህንድስና ዲዛይን ለማከናወን ከተመረጠው ማህንድራ ከተባለ የህንድ አማካሪ ድርጅት ጋር የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ባለፈው ግንቦት ወር ውል ፈርሞ በአሁኑ ወቅት ረቂቅ ዲዛይኑ ተዘጋጅቶ ለምርመራ ቀርቧል፡፡

በፓርኮቹ የሚቋቋሙት መሠረተ ልማቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ዝርጋታዎች፣ የፈሳሽና የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመሮች፣ ሞዴል የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያና ማምረቻ ሕንፃዎች፣ የማቀነባበሪያና ማምረቻ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችና መገልገያዎች መትከያ ሕንፃዎች፣ የጥሬ ዕቃዎችና የምርት መጋዘኖች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ፣ የአስተዳደር ቢሮ ሕንፃዎች፣ የባንክ፣ ኢንሹራንስ፣ የማሪታይም፣ የትራንዚት አገልግሎት ቢሮዎች፣ የሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤቶች ሕንፃዎች፣ የሠራተኞች ማሠልጠኛ ማዕከል፣ የመዋዕለ ሕፃናትና ትምህርት ቤት፣ አረንጓዴ ቦታዎችን እንደሚያጠቃልል ዶ/ር መብራህቱ ገልጸው፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል ወደ ክልሎች እንዲሳብ በተቻለ መጠን ሁሉም አገልግሎቶች የተሟሉበት ምቹ የሥራና መኖሪያ ቦታ እንደሚፈጠር ተናግረዋል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ ያለውን ፍልሰት ለመቀልበስ፣ ወደ ውጭ የሚደረገውን ስደት ለማስቀረት መንግሥት ሰፊ ሥራ እየሠራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በፓርኮቹ እንደየአካባቢያቸው የግብርና ምርቶች ሁኔታ የጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ የዶሮና የከብት ሥጋ፣ የወተት፣ የማር፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የቡና ፋብሪካዎች እንደሚቋቋሙ ገልጸዋል፡፡

ለእያንዳንዱ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ 50 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክና 6,000 ሜትር ኩብ ውኃ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል፡፡ የፓርኮቹ ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅም ሲሠሩ ከቡሬ ፓርክ በዓመት 558,000 ቶን መጠን ያላቸው የተለያዩ ምርቶች እንደሚመረቱና 14 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚገኝ፣ ከባከር ፓርክ 700,000 ቶን መጠን ያላቸው የተለያዩ ምርቶች እንደሚመረቱና 18 ቢሊዮን ብር ሽያጭ እንደሚገኝ፣ ከቡልቡላ ፓርክ 591,000 ቶን ምርትና 14 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚገኝ፣ ከይርጋለም ፓርክ 233,000 ቶን ምርትና ስድስት ቢሊዮን ብር ሽያጭ እንደሚገኝ ተገምቷል፡፡ እያንዳንዱ ፓርክ 419,000 ቀጥተኛ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር፣ በተዘዋዋሪ ደግሞ ለ210,000 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ታቅዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ባለሀብቶች መሬት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ሌሎች መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያታክታቸውን ውጣ ውረድ በማስቀረት በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡና ሥራቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲሠሩ እንደሚያስችል እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር መብራህቱ፣ ከዚህ በኋላ በተበታተነ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ልማት እንደማይካሄድ አስረድተዋል፡፡ ‹‹በተበታተነ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ልማት ማካሄድ የአገር ሀብት ማባከን ነው፡፡ መሬት ውድ ነው፡፡ መሠረተ ልማት በተለያዩ ቦታዎች ማሟላት ለመንግሥት አስቸጋሪ ነው፡፡ ባለሀብቱም ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ቦታ ማግኘት ሲችል በተለያዩ ቦታዎች መንከራተት አላስፈላጊ የሀብትና ጊዜ ብክነት ያስከትላል፡፡ ስለዚህ የምናስተላልፈው መልዕክት ለማልማት ዕቅድ ያለው ወይም መንገድ ላይ ያለ ሁሉም ባለሀብት ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲገባ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አክለውም መንግሥት በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች መካከል ጋብቻ ለመፍጠር ጥረት ላይ መሆኑን፣ ሕንፃ ሠርቶ ማከራየት ወይም ሆቴል መገንባት ዘላቂ ልማት እንደማያመጣ፣ በቀጣይ ሀብት ለመፍጠርና ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥረው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሆኑ ባለሀብቶች በዚህ ዘርፍ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሚገቡ ባለሀብቶች መንግሥት የባንክ አገልግሎትና ሌሎች ድጋፎች እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

ከየካቲት ወር ጀምሮ ወደ አግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ለሚገቡ ኩባንያዎች የሚያስፈልጉ መሥፈርቶች ተዘርዝረው በሚዲያ እንደሚገለጽ፣ አልሚዎች ከመስከረም 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ፓርኮቹ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

በተያያዘ ዜና ከውጭ የሚገቡ የምግብና የመጠጥ ምርቶችን የአገር ውስጥ አምራቾች በአገር ውስጥ ምርቶች እንዲተኩ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲቲካልስ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል ባዘጋጁት የምክክር መድረክ ላይ፣ ከውጭ ለሚገቡ ምግብ ነክ ምርቶች አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንደምታወጣ ተገልጿል፡፡ በአገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ የዶሮና የከብት ሥጋ፣ ወተት፣ ዓሳ፣ ጭማቂዎችን ሆቴሎች፣ ሱፐር ማርኬቶችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ እንደሚገዙ ተገልጿል፡፡ ‹‹እንደ ደም ጠብታ የሚያስፈልገንን የውጭ ምንዛሪ ያላግባብ እያባከንን ነው፤›› ያሉት ዶ/ር መብራቱ፣ ‹‹የግብርና ምርት ጠፍቶ ሳይሆን እሴት ጨምሮ ማቀነባበር ስላቃተን ጥሬውን እንልካለን፡፡ አንዳንድ አገሮች የራሳችንን ምርት ጥሬውን ወስደው አቀነባብረው መልሰው ይሸጡልናል፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ምግብ ዝግጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ሀብቱ፣ አየር መንገዱ በበረራ ወቅት ለሚቀርቡ ምግብና መጠጦች ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችና ተያያዥ ምርቶች ግዥ በዓመት 100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግ፣ ከዚህ ውስጥ 90 በመቶ ከውጭ ተገዝተው እንደሚገቡና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የሚያቀርቡት አሥር በመቶ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምግብ ዝግጅት ክፍል 600 ዓይነት ምርቶች ግዥ እንደሚፈጽም፣ ከእነዚህ ውስጥ 120 የሚሆኑት ምርቶች የአገር ውስጥ አምራቾች እንደሚያቀርቡ፣ 55 ያህል የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ከአየር መንገዱ ጋር አብረው እንደሚሠሩ አቶ አክሊሉ ተናግረዋል፡፡

ሐበሻ ቢራ፣ ፋሚሊ ወተት፣ ካስትል ዋይን፣ መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች የኅብረት ሥራ ማኅበርና በሞጆ ከተማ የሚኘው ሉሜ አዳማ የዱቄት ፋብሪካ በአርአያነት ተጠቅሰዋል፡፡

አየር መንገዱ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ማር፣ ወተት፣ የተለያዩ ጭማቂዎች፣ የከብትና የዶሮ ሥጋ፣ ማር ማራታና ሌሎች በርካታ ምርቶች ከአገር ውስጥ አምራቾች መግዛት እንደሚፈልግ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ተቀራርቦ መሥራት ፍላጎቱ እንደሆነ አቶ አክሊሉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የእኛ ፍላጎት ከምንፈልጋቸው ምርቶች 80 በመቶ ከአገር ውስጥ ኩባንያዎች መግዛት ነው፤›› ያሉት አቶ አክሊሉ፣ የምግብ ማቅረቢያና መመገቢያ ዕቃዎች (ማንኪያ፣ ሹካና ኩባያዎች) የፕላስቲክ ዕቃዎች በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወጪ እየተደረገ ከውጭ እንደሚያስገባ፣ ነገር ግን እነዚህ ምርቶች በአገር ውስጥ ፕላስቲክ አምራቾች ሊመረቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ ‹‹እኛ የምንፈልገው ጥራት፣ ብዛትና ቀጣይነት ያለው አቅርቦት ነው፡፡ ዛሬ አቅርቦ በሚቀጥለው ሳምንት አልችልም ማለት እኛ ዘንድ አይሠራም፡፡ በዋጋም ተወዳዳሪ መሆን ይኖርባችኋል፡፡ አስፈላጊውን ዝርዝር መረጃ በስልክም በአካልም መጥታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤›› ብለዋል፡፡ የተለያዩ የምግብና የመጠጥ አምራቾች ከአየር መንገዱ ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው አየር መንገዱ የሚፈልጋቸውን የምርት ዓይነቶች ዝርዝር፣ የጥራት ደረጃ መሥፈርቶች፣ የምርት ምርጫ መመዘኛዎቹን እንዲያሳውቃቸው ወይም መረጃዎቹን የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻችላቸው ጠይቀዋል፡፡

አምራቾቹ የመሬት፣ የፋይናንስና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግሮች እንዳሉባቸው ተናግረዋል፡፡ በጉምሩክ፣ በታክስ አሠራር፣ በጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ አገልግሎቶች ላይ ችግር የገጠማቸውም ኩባንያዎች አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ የምርት ማሸጊያ ዕቃዎች እጥረትም እንዳለ ተገልጿል፡፡ የተዘረዘሩትን ችግሮች መንግሥት እንደሚመለከታቸውና መፍትሔ ለመስጠት እንደሚሞክር፣ የምክክር መድረኩ በቀጣይነትም እንደሚዘጋጅ ከመድረክ መሪዎቹ ተገልጿል፡፡ 

Standard (Image)

ንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምክር ቤቱን ጠቅላላ ጉባዔ አገደ

$
0
0

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ሊያካሂደው የነበረው ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ እንዲቆይ ንግድ ሚኒስቴር ውሳኔ ላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡  

ለተከታታይ ወራት ውዝግብ ሲፈጥር የነበረው በንግድና ምክር ቤት ውስጥ እየታየ ያለው የሕግ ጥሰትና ተፈጸሙ የተባሉ ሕገወጥ ተግባራት እስኪጣሩ ድረስ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ሊካሄድ የነበረው ጉባዔና ምርጫ እንዲታገድ የተወሰነው ማክሰኞ ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. መሆኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ንግድ ሚኒስቴር እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ ቀደም ብሎ በንግድ ምክር ቤቱ አንዳንድ አባላት መረጃዎች ሲቀርብለት የነበረ ቢሆንም፣ ጣልቃ ላለመግባትና ጉዳዩ በንግድ ምክር ቤቱ እንዲቋጭ ሲመክር መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የንግድ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጥር 30 ቀን ሊካሄድ የነበረው ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ ታግዶ እንዲቆይ የሚገልጽ ብቻ ሳይሆን፣ ተፈጠሩ የተባሉትን ችግሮች በራሱ መንገድ ለማጣራት መወሰኑንም ያመለክታል፡፡

በንግድ ምክር ቤቱና በአባል ምክር ቤቶች መካከል በተፈጠረ የሐሳብ ልዩነት ጠቅላላ ጉባዔውን ምርጫ ለማካሄድ ባለማስቻሉ፣ ችግሩን ለመፍታት 18 አባል ምክር ቤቶች አጣሪ ግብረ ኃይል እስከማቋቋም መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡

ሆኖም አሁን እየታየ ያለው ችግር እየገዘፈና ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ፣ ከጠቅላላ ጉባዔውና ከምርጫው በፊት ንግድ ሚኒስቴር እጁን ለማስገባት እንደተገደደ የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በ18 አባል ምክር ቤቶች ተቋቁሞ የነበረው አጣሪ ኮሚቴም የተፈጠሩ የሕግ ጥሰቶች ካሉ እንዲመረመሩ የሁለት ወራት ጊዜ ወስዶ ሲሠራ ከቆየ በኋላ፣ ሕግ በጣሱት ላይ ዕርምጃ ይወሰድ የሚል ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡

በዚህ መሠረት በተለይ ከታች ሳይመረጡ በላይኛው እርከን የተመረጡ አመራሮች ካሉ ይህ ተጣርቶ ውሳኔ ይሰጥበት ብሎ የመጨረሻው ውሳኔ እየተጠበቀ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደ አመራር ለመምጣት የአባሎቻቸውን ቁጥር ከፍ በማድረግ የቀረቡ አሉ በመባሉም ይህም ጉዳይ እንዲጣራ ውሳኔ ተላልፎ ነበር፡፡

በዚህም ውሳኔ መሠረት በተደረገ ማጣራት ከ500 ሺሕ በላይ አባላት አለን ብለው ያስመዘገቡ አባል ምክር ቤቶች፣ በትክክል አባል መሆናቸውን የሚያረጋግጥና ንግድ ፈቃድ ሊቀርብባቸው ያልቻሉ ከ100 ሺሕ በላይ አባላት ተገኝተዋል፡፡ እንዲህ ያሉ መረጃዎች እየተጠናከሩ ባለበት ወቅት ተጨማሪ የሕግ ጥሰቶች በአንዳንድ የምክር ቤቱ አመራሮች እየታየ በመምጣቱ፣ ጉባዔውም ለማካሄድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው ተብሎ ነበር ንግድ ሚኒስቴር የዕገዳ ውሳኔ ላይ የደረሰው፡፡

Standard (Image)

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርምራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ታወቀ

$
0
0

- በቅርቡ የተከሰተው የግምጃ ቤት ቃጠሎ ለፕሬዚዳንቱ መታሰር ምክንያት መሆኑን ዪኒቨርሲቲው ይገልጻል

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አቶ አደም ቦሪ ከሐሙስ ጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲውን ለስድስት ዓመታት ያህል መምራታቸው የተገለጸው አቶ አደም፣ ለእስር ያበቃቸው ጉዳይ ምን እንደሆነ ሪፖርተር በተለያየ መንገድ ለማጣራት ሙከራ ቢያደርግም፣ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት አልቻለም፡፡ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ መሐመድ አሎፍኪኤን አቶ አደም መታሰራቸውን ከማረጋገጥ በስተቀር ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ይሁንና አቶ አደምን ለእስር እንዳበቃቸው ከሚጠቀሱ ጉዳዮች መካከል ከሁለት ሳምንት በፊት በዩኒቨርሲቲው የተከሰተው የመጋዘን ቃጠሎ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ጉዳዮችና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡበከር አሊ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አቶ አደምን ለእስር እንዳበቃቸው ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተገለጸውና ክስ እንዲመሠረትባቸው ምክንያት የሆነው፣ በቃጠሎው ምክንያት የተደረሰበትን የምርመራ ውጤት እንዲገለጽላቸው መጠየቃቸው ነው፡፡ የቃጠለው መንስዔ ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ተግባር እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚያሚን ሲገለጽ፣ በአንፃሩ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርምራ ክፍል ግን ከዚህ የተለየ ውጤት እንዳለው እንደሚገመት መላምቶች እየተደመጡ ነው፡፡ መላምቶቹን የጠቀሱት አቶ አቡበከር  የሚመሩት ተቋም ምርመራ እየተካሄደበት እንደመሆኑ መጠን ፕሬዚዳንቱ የምርመራ ውጤቱ ከምን እንደደረሰ የመጠየቅና የማወቅ መብት እንዳላቸው ተከራክረዋል፡፡  አቶ አቡበከር ይህን ቢሉም አቶ አደም ላይ  ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ግምጃ ቤት ቃጠሎ ጋር ይያያዛል ቢባልም ለአቶ አደም መታሰር እየተነገሩ ያሉት ምክንያቶች ግን ከዚህም የላቁ ናቸው፡፡ ከግንባታና ከግዥ ሒደቶች ጋር የተያያዙ የሙስና ወንጀሎች ለፕሬዚዳንቱ መታሰር ምክንያት እንደሆኑ ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስለፕሬዚዳንቱ መታሰር ማብራሪያ እንዲሰጡ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢና የአርብቶ አደሮችና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አወል ዋግሪስን ሪፖርተር አነጋግሮ፣ ስለጉዳዩ በማጣራት ላይ እንደሚገኙና የደረሰቡበትን ውጤት እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡

በፕሬዚዳንቱ መታሰር ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ እንዲሰጥበት በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍን የሚመሩትና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል የሆኑትን ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ሪፖርተር ለማነጋገርና ማብራሪያ ለማግኘት ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ ዘርፍ ስለቃጠሎው ጉዳይ የደረሰበትን ውጤት ለማወቅ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ይሁንና የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ ማካሄዳቸውን ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከተመሠረተ ዘጠኝ ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሰባት ኮሌጆችና 34 የትምህርት ክፍሎችን አዋቅሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የተቋሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የቅበላ አቅሙ በመደበኛው የትምህርት መርሐ ግብር ከ4,000 በላይ፣ በማታው ክፍለ ጊዜ ከ1,000 በላይ፣ እንዲሁም በክረምት ወራት ከ1,500 በላይ ተማሪዎችን ለማስተናገድ የሚችልበት አቅም ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ሪፖርተር ለኅትመት ማክሰኞ ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት እስከገባበት ድረስ አቶ አደም ከእስር አልተለቀቁም፡፡ 

 

 

 

Standard (Image)

የ28ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና አዳዲስ ክስተቶች

$
0
0

-  ኢትዮጵያ ከግብፅና ከደቡብ ሱዳን ጋር ያደረገችው ቆይታ

-  ለኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር የተጠበቁት ዕጩ አለመመረጥ

-  የሞሮኮ ከ33 ዓመታት በኋላ ወደ ኅብረቱ መመለስ

-  ዶ/ር ድላሚኒ ዙማ ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንትነት መወዳደር

የአፍሪካ ኅብረት 28ኛው የመሪዎች ጉባዔ ከሰኞ ጥር 22 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲከናወን፣ ከወትሮ ለየት ያሉ አዳዲስ ክስተቶች ታይተውበታል፡፡ ዋና ዋና ከተባሉት ክስተቶች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ለጉባዔው አዲስ አበባ ከተገኙት የግብፅ ፕሬዚዳንት አቡዱልፈታህ አልሲሲና ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ መወያየታቸው አንዱ ነው፡፡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ይመረጣሉ ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር አሚና መሐመድ ወድቀው፣ የቻድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሳ ፋቂ መሐማት መመረጣቸው ሁለተኛው ክስተት ነው፡፡ ሦስተኛው ሞሮኮ እ.ኤ.አ. በ1984 ሯሳን ከቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አግልላ ከቆየች ከ33 ዓመታት በኋላ መመለሷ ነው፡፡ አራተኛው ክስተት የኅብረቱን ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚያስረክቡት ዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪ ይሆናሉ መባሉ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ ሳቢያ በተከሰተው ቀውስ ከጀርባ የግብፅ ተቋማት እጅ እንዳለበት በመንግሥት ከተገለጸ በኋላ፣ በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው ግንኙነት የበለጠ ውጥረት ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የግብፅ መንግሥትን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ መጠየቁ ለተፈጠረው ውጥረት በምክንያትነት ተወስቷል፡፡ በ28ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተገኙት የግብፅ ፕሬዚዳንት ከጠቅላይ  ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር የነበራቸው ቆይታ ፍሬያማ ነበር ተብሏል፡፡ በተለይ ሁለቱ መሪዎች በጎንዮሽ ባደረጉት ውይይት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር መተማመን መፍጠር እንደሚያስፈልግ፣ የአካባቢውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፀጥታ ትብብር በማጠናከር የሁለቱን አገሮች ወንድማማችነት የሚጎዳ ማንኛውንም ዓይነት ድርጊት መቆጣጠርና መገደብ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ አማካይነት በትብብር የመሥራት አስፈላጊነት፣ በሁለቱ አገሮችና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በመሪዎችና በተቋማት ደረጃ መረጃ በመለዋወጥ ተከታታይ ምክክሮች ማድረግ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን የበለጠ ለማሳደግ፣ የመገናኛ ብዙኃንም ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ መደረግ እንዳለበት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ ስትራቴጂካያዊ ግንኙነታቸውን የሚጎዱ ማናቸውንም ችግሮች በጋራ ለመከላከል መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

የሁለቱ አገሮች መንግሥታት ውጥረት ውስጥ እንዳሉ በሚነገርበት በዚህ ወቅት፣ በዲፕሎማሲያዊ አቀራረብ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረው መግባባት ላይ መድረሳቸው እንደ አዲስ ክስተት ታይቷል፡፡ በተለይ ደግሞ ሁለቱ መሪዎች በቋሚነት በተለያዩ ጊዜያት በሁለቱ አገሮች ጉብኝት ለማድረግ መስማማታቸው፣ ይህንንም ከወዲሁ ለመጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በቅርቡ ግብፅን እንዲጎበኙ በፕሬዚዳንት አልሲሲ ተጋብዘዋል፡፡ በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ባለሥልጣን የተመራ ልዑክ የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጎብኘቱ በግብፅ መገናኛ ብዙኃን ከመጠን በላይ በመራገቡ፣ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ከድጡ ወደ ማጡ ያደርገዋል ተብሎ መሠጋቱ አይዘነጋም፡፡ አሁን ከሁለቱ መሪዎች የተሰማው የመግባባት መግለጫ ግን ሥጋቱን ረገብ ያደረገው መስሏል፡፡

በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን መካከል የነበረውን መልካም ግንኙነት ያበላሸዋል የተባለው ሰሞንኛ ክስተት፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በቅርቡ ወደ ካይሮ አቅንተው ፀረ ኢትዮጵያ ስምምነት አድርገው ተመልሰዋል የሚል ዜና መሰማቱ ነበር፡፡ ለኅብረቱ 28ኛ የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኪር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ከተወያዩ በኃላ የተናፈሰውን ወሬ አስተባብለዋል፡፡ ሁለቱን አገሮች በተመለከተ ማንኛውም ዓይነት ወሬ ቢናፈስ ተቀራርበው ለመነጋገር ምንም አያዳግታቸውም ካሉ በኋላ፣ ‹‹ግንኙነታችን ግን ተጠናክሮ ይቀጥላል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹በመሠረተ ቢስ ወሬ ምክንያት ግንኙነታችን እንዲጎዳ አንፈልግም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ፕሬዚዳንት ኪር ኢትዮጵያን በቅርቡ እንዲጎበኙ የጋበዙ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱም ግብዣውን በደስታ መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡ በንግድና ኢንቨስትመንት በመሠረተ ልማት፣ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን ሁለቱ መሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካዊቷ ዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማን በአዲስ ተመራጭ ለመተካት በተካሄደው ምርጫ ያልተጠበቀ ውጤት ተገኝቷል፡፡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የተወዳደሩት ኬንያዊቷ ዶ/ር አሚና መሐመድ፣ ቦትስዋናዊቷ ፔሎኖሚ ቬንሰን ሞታይ፣ ቻዳዊው ሙሳ ፋቂ መሐማት፣ ኢኳቲሪያል ጊኒው አጋፒቶ ምባ ሞካይና ሴኔጋላዊው አብዱላዩ ባዚላይ ነበሩ፡፡ ከዕጩ ተወዳዳሪዎቹ መካከል ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ለኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሐመድ ቢሆንም፣ ቻዳዊው ሙሳ ፋቂ መሐማት በድምፅ ብልጫ አሸንፈዋል፡፡ ዕጩዎችን ለመምረጥ ሰባት ዙር ምርጫ ተካሂዶ በመጨረሻው የቻድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ላለፉት አራት ዓመታት የኅብረቱን ኮሚሽን በሊቀመንበርነት ከመሩት ዶ/ር ድላሚኒ ዙማ የኮሚሽን ሊቀመንበርነት ተረክበዋል፡፡ በዚህ ምርጫ የፈረንሣይኛ ተናጋሪ አገሮች ተፅዕኖ በማየሉ ምክንያት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከፍተኛ ልምድ የነበራቸው ኬንያዊቷ ዶ/ር አሚና ተሸንፈዋል፡፡ ለኬንያዊቷ መሸነፍ የተለያዩ ምክንያቶች ቢሰጡም፣ እሳቸውን ለማስመረጥ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት የኬንያ መንግሥት ባለሥልጣናት በሞሮኮና በሰሃራዊት ዓረብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መካከል መዋለላቸው መንስዔ መሆኑን ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማቶች መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ከሁለቱ ባላንጣ ወገኖች ለአሚና ይገባ የነበረው ድምፅ ወደ ቻዱ ዕጩ ሳይሄድ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

የ56 ዓመቱ ሙሳ ፋቂ መሐማት በመጨረሻው ዙር 39 ድምፅ በማግኘት 54 አገሮች አባል የሆኑበትን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ጨብጠዋል፡፡ ዶ/ር ድላሚኒ ዙማ ደግሞ አዲስ አበባን ከለቀቁ በኋላ በቀጣዩ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንትነት ምርጫ በመወዳደር የቀድሞ ባለቤታቸውን ጃኮብ ዙማ መንበር ለመቆናጠጥ እንዳሰቡ ተሰምቷል፡፡ ዶ/ር ድላሚኒ ዙማ በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ውስጥ ተሰሚነት ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ የኅብረቱን ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ካስረከቡ በኋላ በኢትዮጵያ ለነበራቸው ቆይታ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ከፍተኛ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለኅብረቱ ጉባዔዎቹ መሳካት ላደረጓቸው ትብብሮች አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮው የመሪዎች ጉባዔ ሌላው ክስተት የሞሮኮ ጉዳይ ነው፡፡ ሞሮኮ ከ33 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመመለስ ባደረገችው እንቅስቃሴ መጠነኛ እንቅፋት ቢገጥማትም በድል ተወጥታዋለች፡፡ ወደ ኅብረቱ አባልነት ለመመለስ በሞሮኮ ጥያቄ ያቀረበችው በሐምሌ 2008 ዓ.ም. በሩዋንዳ ኪጋሊ ተካሂዶ በነበረው የመሪዎች ጉባዔ ነው፡፡ በአዲስ አበባው የአሁኑ የመሪዎች ጉባዔ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጥያቄውን የመረመረው በከፍተኛ ክርክር ታጅቦ ነበር፡፡ በተለይ ደቡብ አፍሪካና አልጄሪያ በሞሮኮ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰሙባት ሲሆን፣ ከ53 አገሮች የ39 አገሮችን ድጋፍ አግኝታ ወደ አባልነቷ ተመልሳለች፡፡ አሥር አገሮች ድምፅ እንዳልሰጧት ታውቋል፡፡

ሞሮኮ እ.ኤ.አ. በ1984 በአዲስ አበባ በተካሄደው የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ውሳኔ አኩርፋ ነበር አባልነቷን የተወችው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የራሷ ግዛት እንደሆነች ለምታስባት ሰሃራዊት ዴሞክራቲክ ዓረብ ሪፐብሊክን የወቅቱ የአፍሪካ ድርጅት በአባልነት መቀበሉ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያ ለ33 ዓመታት ከመድረኩ የጠፋቸው ሞሮኮ ከዚህ ጉባዔ በፊት ባደረገችው ቅስቀሳና የማግባባት ዲፕሎማሲ ሥራ ፍላጎቷን አሳክታለች፡፡ በተለይ ባለፈው አንድ ዓመት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በንጉሧ መሐመድ ስድስተኛ የተደረጉ ጉብኝቶችና የኢንቨስትመንት ስምምነቶች የዚህ ጥረት ማሳያ ናቸው ተብሏል፡፡ ሞሮኮ ወደ አፍሪካ ኅብረት በመመለስ ተፅዕኖ ፈጣሪ አገር ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት በስፋት ይነገራል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት 28ኛው የመሪዎች ጉባዔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ በተለይ ተሰናባቹ የኅብረቱ ሊቀመንበር የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከአሁን በኋላ በአፍሪካ የሚደረጉ ምርጫዎች ለዜጎች ሥጋት መፍጠር አይኖርባቸውም ብለዋል፡፡ አዲሱ ተመራጭ ሊቀመንበር የጊኒ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ደግሞ የኅብረቱን ተደማጭነት ለመጨመርና ድምፁን ለማስተጋባት ጥረት እንደሚያደርጉ በንግግራቸው ገልጸው፣ አፍሪካ በአንድ ድምፅ መናገር እንጂ መከፋፈል እንደሌለባት ኮንዴ አሳስበዋል፡፡ በአባል አገሮች መካከል ትብብር እንዲጠናከር፣ ለ700 ሚሊዮን አፍሪካዊያን የኢነርጂ ልማት እንደሚያስፈልግና በወጣቱ ላይ ኢንቨስት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡  

በዘንድሮው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ በክብር እንግድነት ከተገኙት መካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒ ጉተሬዝና የፍልስጤም ፕሬዚዳንት መሐመድ አባስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡  

 

Standard (Image)

በንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ችግር በፈጠሩ ላይ ዕርምጃ ሊወሰድ ነው

$
0
0

በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ውስጥ ተፈጠረ የተባለውን ችግር ለማጣራት በሳምንቱ መጀመርያ ላይ የንግድ ምክር ቤቱን ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ ያገደው ንግድ ሚኒስቴር፣ ለችግሩ መንስዔዎች ናቸው ባላቸው የንግድና ዘርፍ ምክር ቤቶች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ መመርያ ሰጠ፡፡

ንግድ ሚኒስቴር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው በመGለው መድረክ በቅርቡ የንግድ ምክር ቤቱን እንዲያጣራ የተመረጠው ግብረ ኃይል ተወካይ፣ አሉ ስለተባሉት ችግሮች ማብራሪያ መስጠታቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Standard (Image)
Viewing all 1275 articles
Browse latest View live