Quantcast
Channel: ተሟገት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

በኢንተርኮንቲኔንታል ባለቤትና በአቶ ገብረዋህድ ባለቤት የዋስትና ጥያቄ ላይ የቀረበው ተቃውሞ ተቀባይነት አገኘ

$
0
0

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ቁጥር 141352 (24 ሰዎች) ተጠርጥረው ከተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል በነፃ የተሰናበቱት የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤትና የአቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ ባለቤት የዋስትና ጥያቄ ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አገኘ፡፡

ከሳሽ ሁለቱ ተከሳሾች ማለትም አቶ ስማቸው ከበደና ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ወዲያው የዋስትና ጥያቄውን በመቃወም ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግለት የጠየቀ ቢሆንም፣ ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ ቀደም ብሎ ያቀረበውን መቃወሚያ እንዲያሻሽል ጠይቋል፡፡

ተከሳሾቹ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በሌለው ሥልጣን ሊቃወምም ሆነ ሊከራከር እንደማይችል ገልጸው፣ እንዲያሻሽል ያቀረበው ጥያቄ ታልፎ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 66 መሠረት በ48 ሰዓታት መለቀቅ እንዳለባቸውና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 13፣ 25 እና 37 መሠረትም የማይጣስ መብታቸው መሆኑን በመግለጽ ተከሳሾቹ ተከራክረው ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ ጥያቄውን ያመነጨው ከክሱ ተነስቶ መሆኑን በመግለጽ፣ ሊመረምረውና ብይን ሊሰጥበት እንደሚገባ በመግለጽ ለመስከረም 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በሰጠው ብይን ለተሻለ የፍትሕ አሰጣጥ ይረዳ ዘንድ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ጥያቄ መቀበል ተገቢ መሆኑን ማመኑን በመግለጽ፣ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የዋስትና መቃወሚያ አቤቱታውን እስከ መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ በጽሕፈት ቤት በኩል እንዲያስገባ፣ ተከሳሾች መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡  

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

Trending Articles