Quantcast
Channel: ተሟገት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

ቦነስና በገንዘብ የሚቀየር የዓመት ዕረፍት ግብር እንዲከፈልባቸው መንግሥት አሳሰበ

$
0
0

ድርጅቶች ለቀጠሯቸው ሠራተኞች የሚከፍሉት ቦነስና በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ የሚለቁ ሠራተኞች ያልተጠቀሙበትን የዓመት ሥራ ፈቃድ ወደ ገንዘብ በሚቀይሩበት ወቅት፣ ግብር የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጻፈው ደብዳቤ ነው ማሳሰቢያውን ያስተላለፈው፡፡

የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ‹‹ማግኘት›› እና ‹‹መቀበል›› ለሚሉት ቃላት የተሰጠው ትርጉም ሁሉንም የገቢ ሰንጠረዦች የሚመለከት እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጠው በጠየቀው መሠረት፣ ሚኒስቴሩ ሁለት ገጽ የደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ‹‹ማግኘት›› እና ‹‹መቀበል›› ለሚሉት ቃላት የተሰጡት ትርጉሞች ሁሉንም የታክስ ሰንጠረዦች የሚመለከቱ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የቦነስ ክፍያ ለሠራተኞቻቸው እንዲፈጸም ውሳኔ የተላለፈው ከሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በኋላ ከሆነ ግብር ከፋዩ ገቢውን እንደተቀበለ የሚቆጠረው ይኸው ውሳኔ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ስለሚሆን፣ ታክሱ የሚሰላው በአዲሱ የገቢ አዋጅ መሠረት መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 40 የአንድ ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ለሁለት የበጀት ዓመት ብቻ የሚተላለፍ መሆኑን፣  በተለያዩ ምክንያቶች የተላለፈ የዓመት ፈቃድ ያለው ሠራተኛ ሥራውን ቢለቅ ወደ ገንዘብ የሚቀየረው የአንድ ዓመት የሥራ ፈቃድ ብቻ እንደሆነ፣ ሚኒስቴሩ ለባለሥልጣኑ የላከው ደብዳቤ ይገልጻል፡፡ በመሆኑም ወደ ገንዘብ እንዲለወጥ የተፈለገው የዓመት ዕረፍት ውሳኔ የተላለፈው ከሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በኋላ ከሆነ በአዲሱ አዋጅ መሠረት ግብር እንዲከፈልበት ያሳስባል፡፡

በዚህ መሠረትም ቀጣሪዎች የተቀጣሪውን ደመወዝና በዚያው ወቅት የተገኘውን ቦነስ ወይም በገንዘብ የተለወጠ የዓመት ፈቃድ አንድ ላይ በማድረግ ከቅጥር የተገኘ ገቢ አድርገው ሊያሰሉት እንደሚገባ ያስገነዝባል፡፡

በቀድሞውም አዋጅም ቢሆን ቦነስና በገንዘብ የተለወጠ የዓመት ፈቃድ ከግብር ውጪ አለመሆናቸውን ነገር ግን መሥሪያ ቤቶች በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የመወጣት ችግር እንደነበረባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡    

 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

Trending Articles