Quantcast
Channel: ተሟገት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ያዕቆብ ያላ የሎጅስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኑ

$
0
0

የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ያዕቆብ ያላ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቶ ያዕቆብን በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ባያካትቷቸውም፣ ግዙፉን የሎጅስቲክስ ኢንተርፕራይዝ እንዲመሩ ሹመዋቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ያዕቆብን ብቻ ሳይሆን፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩን አቶ አህመድ ሺዴ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርገው ሹመዋል፡፡

አቶ አህመድ ቀደም ሲል የትራንስፖርት ሚኒስትርና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩትን፣ በአሁኑ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙትን ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን ተክተዋል፡፡

አቶ ያዕቆብ ደግሞ ለአምስት ዓመታት የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ አህመድ ቱሳን ተክተዋል፡፡ አቶ አህመድ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የቀድሞው ዋና ዳይሬክተርና አዲሱ የቦርድ ሰብሳቢ ማክሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ከኢንተርፕራይዙ ሥራ አመራር ቦርድና ከማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅና ምክክር ማድረጋቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ ያዕቆብ ግን ከአዲስ አበባ ውጪ ስለነበሩ አልተገኙም፡፡

አቶ ያዕቆብ ለበርካታ ዓመታት በቀድሞው ግብርና ሚኒስቴር ሠርተዋል፡፡ አቶ ያዕቆብ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ምርቶች ግብይት ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ መንግሥት በዘርፉ ለውጥ ለማድረግ የግብርና ግብይቶች በንግድ ሚኒስቴር ሥር እንዲካሄድ ሲያደርግ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሠርተዋል፡፡ በኋላም በንግድ ሚኒስትርነት ቆይተው፣ መንግሥት እንደ አዲስ ካቢኔውን ሲያዋቅር ቦታቸውን ለዶ/ር በቀለ ቡላን ለቀዋል፡፡

አቶ ያዕቆብ የሦስት ድርጅቶች ውህድ የሆነውን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ይመራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዕቃ የማጓጓዝ አቅሙ በየጊዜው እያደገ ሲሆን፣ በ2008 ዓ.ም. 175 ሺሕ ኮንቴይነሮችን አጓጉዟል፡፡ በገቢ ደረጃም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 16.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ታውቋል፡፡

 

 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 1275

Trending Articles