የጂቡቲ መንግሥት ለኢትዮጵያ የመደበውን የነዳጅ ዴፖዎች መጠን እንዲጨምር ሊጠየቅ ነው
የጂቡቲ መንግሥት ለኢትዮጵያ የመደበውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፓዎች መጠን እንዲጨምር የማግባባት ሥራ እንደሚያከናውን የማዕድን፣ ተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በጂቡቲ የነዳጅ ወደብ የሚገኙ ዴፓዎች ኢትዮጵያ ከምታስገባው የነዳጅ መጠን ጋር ማጣጣም...
View Articleየሐዋሳና ሰመራ ኤርፖርቶች ተርሚናል ግንባታ ለአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ተሰጠ
የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የሐዋሳና የሰመራ ኤርፖርቶች የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃዎች ግንባታ ለሁለት አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ሰጠ፡፡የሐዋሳ ኤርፖርት ተርሚናል ግንባታ ኤፍኢ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በ126,534,721 ብር ለማካሄድ ጨረታውን ያሸነፈ ሲሆን፣ የሰመራ ኤርፖርት ተርሚናልን ግንባታ ደግሞ...
View Articleየመንግሥትና የግል ኢንቨስትመንት አጋርነትን የሚቆጣጠር ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው
- ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን ይጠበቃልየመንግሥትና የግል ኢንቨስትመንት አጋርነትን የሚመራና የሚቆጣጠር ኤጀንሲ ለማቋቋም፣ የሕግ ማዕቀፍ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡እንደ ምንጮች ገለጻ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት...
View Articleየውኃ ልማት ፈንድ ለ35 የገጠር ከተሞች የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ፕሮጀክቶች የሚውል የ75 ሚሊዮን ዩሮ ብድር አገኘ
- ስምንት ከተሞች 188 ሚሊዮን ብር ብድር ተሰጣቸውየውኃ ሀብት ልማት ፈንድ 35 የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ለማድረግ የሚያስችል 75 ሚሊዮን ዩሮ ወይም የ1.8 ቢሊዮን ብር ብድር ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ ከአውሮፓ...
View Articleየመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ግንባታ እንዲመለስ ተወሰነ
ከቀድሞው መንግሥት ውድቀት በኋላ ከመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ውጭ የተደረገው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ከ25 ዓመታት ረጅም ቆይታ በኋላ ወደ ግንባታ መግባት የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ፡፡የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዓርብ ጥር 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ አደረጃጀቱ ተለውጦ ‹‹የፌዴራል...
View Articleኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ከምትችለው በአሥር በመቶ እያቀረበች መሆኗ በጥናት ተመለከተ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ40 በላይ ለሆኑ ያላደጉ አገሮች የንግድ ዘርፍ ማሳደጊያ ድጋፍ እየሰጠ የሚገኘው የተቀናጀ የንግድ ማሳደጊያ ተቋም፣ ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ከምትችለው የምርት መጠን ውስጥ ከአሥር በመቶ ያነሰውን በማቅረብ ላይ እንደምትገኝ በጥናት አመለከተ፡፡ በዓለም ንግድ ድርጅት አስተባባሪነት፣ በስድስት...
View Articleአወዛጋቢ ሆኖ የቆየውን የሊዝ አዋጅ ለማሻሻል ረቂቅ ተዘጋጀ
በትልልቅ ከተሞች ሥር ሰዶ የቆየውን የመሬት አስተዳደር ችግር ለመፍታት፣ ኅዳር 2004 ዓ.ም. የፀደቀው የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721 በድጋሚ እንዲሻሻል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ከጥንስሱ ጀምሮ አወዛጋቢ የነበረው የሊዝ አዋጅ የማያሠሩ አንቀጾች እንደነበሩትና ከወዲሁ መስተካከል እንዳለበት...
View Articleየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከቀነ ገደቡ አስቀድሞ እንደማይነሳ መንግሥት አስታወቀ
- ቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት በሙሉ ሥልጠና ወስደው ተለቀዋል- አሜሪካ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያዊያንን የምታባርር ከሆነ መንግሥት እጄን ዘርግቼ እቀበላለሁ አለ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን ሰላማዊ ሕይወት እንዳስጠበቀና ከቀኑ ገደቡ...
View Articleበፋይናንስ ፍሰት መስተጓጎል የኮንዶሚንየም ቤቶች ግንባታ ችግር እንደገጠመው ተጠቆመ
የመኖሪያ ቤቶችን ችግር ለመፍታት በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመሩ የ20/80 እና የ40/60 ቤቶች ግንባታ፣ በፋይናንስ ፍሰት በኩል መስተጓጎል በመፈጠሩ የቤቶቹ ግንባታ ችግር እንደገጠመው ተጠቆመ፡፡የቤቶች ግንባታ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት በሺሕ የሚቆጠሩ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ድርጅቶች፣...
View Articleሔኒከንና ካንጋሮ ፕላስት ሲወዛገቡበት የነበረው የንግድ ምልክት እንዳይሰረዝ ውሳኔ ተሰጠ
ካንጋሮ ፕላስት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከስድስት ዓመታት በፊት በአዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት አስመዝግቦት የነበረውን ‹‹አይቤክስ›› የንግድ ምልክት፣ በሔኒከን ብሪዌሪስ አክሲዮን ማኅበር አመልካችነት ጽሕፈት ቤቱ ሰርዞት የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ፍርድ ቤት እንዳይሰረዝ ውሳኔ ሰጠ፡፡የአዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት...
View Articleበኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የቱርካውያን ትምህርት ቤቶች ለቱርክ መንግሥት እንደሚተላለፉ ፕሬዚዳንት ሙላቱ አስታወቁ
- የትምህርት ቤቶቹ ባለሀብቶች ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ንክኪ እንደሌላቸው እየገለጹ ነውበኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት ሲንቀሳቀሱ የቆዩትንና በቱርክ መንግሥት አሸባሪ ከተባለው የጉለን ንቅናቄ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የቱርካውያን ባለሀብቶች ትምህርት ቤቶችን፣ ለቱርክ መንግሥት አሳልፎ እንደሚሰጥ ፕሬዚዳንት ዶ/ር...
View Articleከ85 ሺሕ በላይ የንግድ ባንክ ኤቲኤም ተጠቃሚዎች የሌሎች ባንኮችን አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲኤም ካርድ ይዘው ከሌሎች ባንኮች ኤቲኤሞች ገንዘብ ለማውጣት ያስችል የነበረው አገልግሎት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መቋረጡ ተገለጸ፡፡ በዚሁ ምክንያት እስከ ዓርብ የካቲት 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ከ85 ሺሕ በላይ የንግድ ባንክ ደንበኞች አገልግሎት ለማግኘት ሞክረው...
View Articleእነ አቶ መላኩ ፈንታ ነፃ በተባሉባቸው የሙስና ክሶች ላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠየቀ
በተጠረጠሩበት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል በሦስት መዝገቦች ክስ የተመሠረተባቸው እነ አቶ መላኩ ፈንታ፣ በመዝገብ ቁጥር 141352 ከቀረቡባቸው 93 ክሶች ውስጥ በስድስት ክሶች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም፣ ውሳኔውን የተቃወመው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠየቀ፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ...
View Articleጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የ‹‹አጐዋ›› ነፃ ንግድ ሥርዓት በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እንዳይቋረጥ ጠየቁ
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለአፍሪካ አገሮች ምርቶች የፈቀደችውን “AGOA” በሚባል መጠሪያ የሚታወቀው ከኮታና ከታሪፍ ነፃ የንግድ ሥርዓት ሊያቋርጡት እንደማይገባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዎል ስትሪት ጆርናል ከተባለው ታዋቂ የአሜሪካ ጋዜጣ ጋር ሰሞኑን...
View Articleኢትዮጵያን ከኬንያና ከሱዳን የሚያገናኙ የባቡር መስመሮችን የውጭ ኩባንያዎች ገንብተው እንዲያንቀሳቀቅሷቸው ታቀደ
- በአዲስ አበባ የታቀዱት ማስፋፊያዎች ከማስተር ፕላኑ ጋር መጣጣም ይጠበቅባቸዋልየኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽን በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከያዛቸው ግዙፍ የባቡር መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል፣ የሞጆ-ሐዋሳ-ሞያሌና የአዲስ አበባ-ጅማ-በደሌ መስመሮችን በራሳቸው ፋይናንስ ገንብተው...
View Articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ ስድስት ቢሊዮን ብር አተረፈ
- በአገሪቱ የተፈጠረው አለመረጋጋት አነስተኛ ተፅዕኖ አሳድሮበታል- ከውጭ አየር መንገዶች የሚገጥመው ፉክክር አሳሳቢ ሆኗልከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ. 2015 እስከ 2016 በጀት ዓመት የተጣራ ስድስት ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ አየር...
View Articleከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዳያስፖራው የባንክና የኢንሹራንስ አክሲዮኖች ለሽያጭ እየቀረቡ ነው
በባንኮችና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ይዘው የቆዩ ከ700 በላይ የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለድርሻዎች መገኘታቸው፣ ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ቀረበ፡፡ የእነዚህ ባለአክሲዮኖችን ድርሻ ለኢትዮጵያውያን በሽያጭ ለማስተላለፍ ባንኮች ጨረታ ማውጣት...
View Articleየከርሰ ምድር ውኃ መንጠፍና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አዲስ አበባን ለውኃ እጥረት ዳረገ
ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ወደ ሥርጭት የገቡ የከርሰ ምድር ውኃ ማመንጫዎች በገጠማቸው ችግር ምክንያት፣ አዲስ አበባ በድጋሚ የውኃ አቅርቦት እጥረት ገጠማት፡፡የችግሩ መነሻ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ቢሾፍቱ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው አቃቂ አካባቢ የተቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶች፣ እንዲሁም ለአጭር...
View Articleከቃሊቲ እስከ ቂሊንጦ የሚገነቡ ሁለት የመንገድ ኮሪደሮች በ4.7 ቢሊዮን ብር ሊጀመሩ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ወጪ ይወጣበታል የተባለው በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚገነባው የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱና የቃሊቲ - ቂሊጦ ሁለት የመንገድ ኮሪደሮች ፕሮጀክት፣ በ4.7 ቢሊዮን ብር ለመገንባት የተስማማው የቻይና ኩባንያ ግንባታውን ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም....
View Articleአምስተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
አምስተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ጉባዔ በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ሼክ መሐመድ አል አሙዲ አምስተኛውን የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ስፖንሰር እንደሚያደርጉት የተገለጸ ሲሆን፣ ከጉባዔው ዋና የመወያያ አጀንዳዎች መካከል የፋይናንስና የካፒታል ኢንቨስትመንት በአፍሪካ የሚለው ትልቅ ትኩረት...
View Article