ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በእስራኤል
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለአምስት ቀናት በእስራኤል የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ከዚህ በፊት የቀድሞው የእስራኤል ፕሬዚዳንት ሽሞን ፔሬዝ ባረፉ ጊዜ ለቀብር ወደ እስራኤል አቅንተው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ ካለፈው እሑድ ጀምሮ በእስራኤል ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ላይ...
View Articleመንግሥትን ከ10.9 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥቷል የተባለ ተጠርጣሪ ታሰረ
የቡና ላኪነት ፈቃድ በማውጣት ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሚገዛውን ቡና ወደ ውጭ መላክ ሲገባው ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለ ቡና ነጋዴ፣ መንግሥትን ከ10.9 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ በማሳጣት ተጠርጥሮ ታሰረ፡፡ተጠርጣሪው ቡና ነጋዴ እምሩ ሙርሺድ መሐመድ የሚባል ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ...
View Articleየኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዳይሬክተሮች ሹመት ውድቅ ተደረገ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማኔጅመንት አማካይነት አዳዲስ ዳይሬክተሮችን ለማሾም ቀርቦ የነበረው ጥያቄ፣ በባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ውድቅ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡በአሁኑ ወቅት ወደ 26 የሚጠጉ በዳይሬክተሮች የሚመሩ ኃላፊነቶች እንዳሉት የሚታወቀው ባንኩ፣ እነዚህ ቦታዎችን በአዳዲስ ሰዎች ለመሙላት ለቦርዱ ጥያቄ...
View Articleየኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዳዲስ የቦርድ አባላት ተሾሙለት
የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በበላይነት የሚመሩ አዳዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሹመት ፀድቆ ሥራ ጀመሩ፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ረዲ አዲሱ የምርት ገበያው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሰይመዋል፡፡ ዘጠኝ አባላት ያሉት የምርት ገበያው የቦርድ አመራሮች ውስጥ አምስቱ በቀጥታ በንግድ...
View Articleግንባታ እያደናቀፉ ነው በተባሉ የፍርድ ቤት ዕግዶች ላይ መፍትሔ እንዲቀርብ ታዘዘ
ግንባታ እያደናቀፉ ነው በተባሉ የፍርድ ቤት ዕግድ ትዕዛዞች ላይ ውሳኔ ለመስጠት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በጋራ እንዲሠሩና የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከለኛውን የከተማው ክፍል በመልሶ ማልማት ፕሮጀክት በድጋሚ...
View Articleየግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አሠራሩን በማስተካከል 2.6 ቢሊዮን ብር አዳንኩ አለ
የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2008 ዓ.ም. ግብርና ምርት ዘመን በተከተላቸው አዳዲስ ማሻሻያዎች፣ 2.6 ቢሊዮን ብር (120 ሚሊዮን ዶላር) ማዳኑን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃን አወቀ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣...
View Articleየቻይና መንግሥት ለአፍሪካ ተልዕኮው በአዲስ አበባ ዋና መሥሪያ ቤት ለመገንባት መሬት ተረከበ
ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአፍሪካ ላይ ፍላጎቱ እያደገ የመጣው የቻይና መንግሥት፣ የአፍሪካ ተልዕኮ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና መሥሪያ ቤቱን ለመገንባት አራት ሔክታር መሬት ተረከበ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቻይና መንግሥትን ፍላጎት ለማሟላት፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ከአፍሪካ ኅብረት ጀርባ የሚገኘው...
View Articleዳኞችንና ዓቃቢያነ ሕጎችን ለመደብደብ ተጋበዙ የተባሉ ተከሳሾች ፍርድ ቤት በመድፈር ወንጀል ቅጣት ተጣለባቸው
የክስ ሒደቱ ለአንድ ዓመት እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ተሰጠከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ጋር በተገናኘ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው 121 ተከሳሾች መካከል 21 ተከሳሾች ዳኞችንና ዓቃቢያነ ሕግን በችሎት ተሳድበዋል፣ ለድብድብም ተጋብዘዋል የተባሉ ‹‹ችሎት በመድፈር ወንጀል›› ጥፋተኛ ተብለው የአንድ ዓመት...
View Articleንግድ ባንክ በሠንጋ ተራ የተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ተረከበ
ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፉት ቤቶች ብዛት 972 መሆናቸው ተጠቆመከ2007 ዓ.ም. መገባደጃ ጀምሮ በቅርቡ እንደየአከፋፈላቸው ይተላለፋሉ እየባለ ላለፉት ሦስት ዓመታት ተመዝጋቢውን ግራ ሲያጋቡ ከነበሩት የክራውንና ሠንጋ ተራ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠንጋ ተራዎችን ሙሉ በሙሉ...
View Articleየሚቀጥለው ዓመት በጀት የ54 ቢሊዮን ብር ጉድለት አለበት
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ለፌዴራል መንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ያቀረቡት 320.8 ቢሊዮን ብር ቀጣይ በጀት፣ 53.9 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አለበት፡፡የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ግንቦት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የበጀት ረቂቅ...
View Articleበኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በዘመኑ ተናኘና ሳሙኤል ጌታቸውእ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ኅብረት የጀርመን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ጆአሺም ሽቺሚት (ዶ/ር) ማረፋቸው ተገለጸ፡፡በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ዶ/ር ጆአሺም ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዳረፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡...
View Articleየባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያ ኃላፊዎች የሚሾሙበት መሥፈርት ሊሻሻል ነው
በዳዊት እንደሻውየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላለፉት አምስት ዓመታት ያህል የባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዋናና ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችን ሹመት ሲመዝንና ሲያፀድቅበት የነበረውን መሥፈርት ሊያሻሽል ነው፡፡ ከሳምንት በፊት ረቂቅ ማሻሻያ መመርያ ለባንክና ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለአስተያየት ቀርቦ ለብሔራዊ ባንክ...
View Articleለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አዳዲስ ኃላፊዎች ተሾሙ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ33.144 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያቋቋመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ሦስት ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎች ተሾሙለት፡፡የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የተሰየሙት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣...
View Articleለሕዝብ ቆጠራ ለሚውሉ ታብሌት ኮምፒዩተሮች ግዥ የ317.5 ሚሊዮን ብር ስምምነት ከሁዋዌ ኩባንያ ጋር ተደረገ
በዳዊት እንደሻውየመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በሚቀጥለው ዓመት ኅዳር ለሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለሚያገለግሉ ታብሌት ኮምፒዩተሮች ግዥ፣ ከቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ጋር የ317.5 ሚሊዮን ብር ስምምነት አደረገ፡፡በስምምነቱ መሠረት ሁዋዌ በጨረታ ከሚገዙት 180 ሺሕ ታብሌት ኮምፒዩተሮችና 126 ሺሕ ፓወር...
View Articleኬንያ በኦሞ ወንዝ ላይ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ተፅዕኖ እንዲጠና ለኢትዮጵያ ጥያቄ አቀረበች
የግልገል ጊቤ ሦስት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብና በኦሞ ሸለቆ የሚካሄዱ የመስኖ ፕሮጀክቶች በቱርካና ሐይቅ ላይ የሚያደርሱት ተፅዕኖ እንዲጠናላት፣ ኬንያ በይፋ ለኢትዮጵያ ጥያቄ አቀረበች፡፡የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጥያቄውን መቀበላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ኬንያ ጥያቄውን ያቀረበችው...
View Article‹‹ኮንትሮባንድ አገሪቱን እየገዘገዛት ነው››
የንግድ ሚኒስትሩባለሥልጣናት ድራማ መሥራት ማቆም አለባቸው ብለዋልየኮንትሮባንድ ንግድ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየገዘገዘ መሆኑን የንግድ ሚኒስትሩ በቀለ ቡላዶ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ሚኒስትሩ የተቋማቸውን የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት፣...
View Articleበዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ተጠየቀ
የአፍሪካ መዲና በመባል በምትታወቀው አዲስ አበባ እያደገ የመጣውን የተሽከርካሪ ብዛት ማስተናገድ እንዲቻልና የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት መንግሥትና የግሉ ዘርፍ በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ተጠቆመ፡፡ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ፕሮግራሞች...
View Articleየቆሼ ተጎጂዎች ማቋቋሚያ ፓኬጅ በተለያዩ ምክንያቶች መጓተቱ ተገለጸ
ከ94.8 ሚሊዮን ብር በላይ ዕርዳታ መሰብሰቡ ተጠቁሟልለቆሼ ተጎጂዎች እንዲውል በተዘጋጀው የማቋቋሚያ ፓኬጅ ያላግባብ ለመጠቀም በገቡ ሰዎች፣ በቤተሰብ መካከል በተነሱ የይገባኛል ጥያቄዎችና ተጎጂዎች መረጃዎቻቸውን በአግባቡ አሟልተው ባለማቅረባቸው በሥራው ላይ መንጓተት እንዲፈጠር ምክንያት መሆናቸው ተገለጸ፡፡ ያላግባብ...
View Articleለሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾች ከቀረጥ ነፃ ዕድል ማሻሻያ ተደረገ
በዳዊት እንደሻውየገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾችን የቀረጥ ነፃ ዕድል አሻሻለ፡፡ከአሁን ቀደም ሚኒስቴሩ ተመላሾችን ለመደገፍ ሲባል ወደ አገራቸው ሲመለሱ ይዘዋቸው ሊመጡ ይችላሉ ተብለው የተገመቱ ወደ 21 የሚጠጉ የቤት መገልገያ ዕቃዎችን፣ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ በሚኒስትሩ በዶ/ር...
View Articleየቀን ገቢ ግምት ከስምንት ሺሕ በላይ ነጋዴዎችን ወደ ሕጋዊ የታክስ ሥርዓት ማስገባቱ ተነገረ
በ2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የቀን ገቢ ግምት ጥናት ከተካሄደ በኃላ 8,651 ነጋዴዎች ወደ ሕጋዊ የታክስ ሥርዓት መግባት መቻላቸው ተገለጸ፡፡በከተማዋ ለዓመታት በነጋዴዎች ዘንድ ጥያቄ ሲያስነሳ የነበረውን ፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት ችግር መስመር ለማስያዝ በ2009 ዓ.ም. በተካሄደው የቀን ገቢ ግምት ጥናት፣...
View Article