ለሞ ኢብራሒም ሽልማት የሚመጥን አፍሪካዊ መሪ አሁንም አልተገኘም
በአፍሪካ የአመራር ስኬት ሽልማት ለመስጠት በማቀድ እ.ኤ.አ. በ2016 በዚሁ ዘርፍ ከሥልጣን የለቀቁ የአፍሪካ መሪዎችን ቢያወዳድርም፣ የወጣውን ከፍ ያለ ደረጃ በማሟላት የሚያሸንፍ መሪ አለመገኘቱን ሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና...
View Articleየግዥ መመርያ በሚጥሱ ነጋዴዎች ላይ የጉዳት ካሳ ቅጣት የሚጥል መመርያ ተዘጋጀ
- የግዥ መርህ የማያከብሩ የሥራ ኃላፊዎችም ይቀጣሉ ተብሏልየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚፈልጓቸውን ዕቃዎች በማዕከል ደረጃ ግዥ እንዲፈጽም የተቋቋመው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት፣ በገቡት ውል መሠረት ዕቃዎችን በወቅቱ በማያቀርቡ ኩባንያዎች ላይ 1.1 በመቶ የተጣራ የጉዳት ካሳ እንደሚያስከፍል ይፋ...
View Articleየሚድሮክ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ
በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ከሚተዳደሩት በርካታ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ (ቲኤንኤ) ኩባንያ ንብረት የሆነ ቤል 222U ሔሊኮፕተር፣ ቅዳሜ የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ አምስት መንገደኞች አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ወደ ሐዋሳ ለመብረር...
View Articleየታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ኃይል ለማመንጨት መቃረቡን መንግሥት ይፋ አደረገ
- ዋናው የውኃ ሙሌት ከታችኛው የተፋሰሱ አገሮች ጋር በመመካከር ይከናወናል ተብሏል - መንግሥት ለሜቴክ ተሳትፎ ያሳለፈው ፖለቲካዊ ውሳኔ ሴራዎችን ማምከኑ ተገለጸ የመሠረት ድንጋዩ ከተጣለ ስድስተኛ ዓመቱን ለመያዝ የተቃረበው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ፣ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ውኃ...
View Articleበግማሽ ዓመት ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 1.2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገለጸ
በተያዘው የበጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የተመዘገበው፣ ከአምናው መሻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት የስድስት ወራቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ35 በመቶ አብላጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡ ለቀጥተኛ...
View Articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጠ
- የህዳሴውን ግድብ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ከኤርትራ መነሳቱ ተጠቆመ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በጄኔቫ (ስዊዘርላንድ) ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሒሩት ዘመኔ ባለፈው ሳምንት...
View Articleአገር በቀል ኩባንያ በ480 ሚሊዮን ብር የአይሲቲ ማዕከል እየገነባ ነው
- መንግሥት የአገር በቀል የአይቲ ኩባንያዎችን አቅም ለመገንባት ጥናት እያካሄደ ነውሲኔት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ የተሰኘ አገር በቀል ኩባንያ በቦሌ ለሚ አይቲ ፓርክ፣ በ480 ሚሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ የአይሲቲ ማዕከል በመገንባት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ...
View Articleጣሊያናዊውን ወጣት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ባለፈው ሳምንት የካቲት 18 ለ19 ቀን 2009 ዓ.ም. አጥቢያ ከሌሊቱ 9፡30 ሰዓት ላይ፣ የ32 ዓመት ጣሊያናዊ ወጣት በጥይት መትቶ ገድሏል የተባለውን ተጠርጣሪ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ ሟች ጃማ ካርሎስ ጉላን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ...
View Articleሐይኒከን በሦስቱም ቢራ ፋብሪካዎቹ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ተከለ
- የቂሊንጦ አካባቢ ነዋሪዎች የሚለቀቀው ፍሳሽ ጉዳት እያደረሰብን ነው አሉየኢትዮጵያ የቢራ ኢንዱስትሪን የተቀላቀለው ሐይኒከን ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ኩባንያ፣ በሦስቱም ቢራ ፋብሪካዎቹ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ማቋቋሙን አስታወቀ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 (ቂሊንጦ) በገነባው ፋብሪካ በ176...
View Articleከ380.6 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ የቡና ነጋዴዎች ተከሰሱ
የተሟላ የቢሮ ዕቃዎችና ወደ ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች ሳይኖሯቸው በአንድ ጉዳይ አስፈጻሚ አማካይነት ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር በመመሳጠር የቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያገኙ ቡና ላኪዎች፣ ከ380.6 ሚሊዮን ብር በላይ ወይም ከ19.8 ሚሊዮን ዶላር በላይ መንግሥትን የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች ክስ...
View Articleዶ/ር መረራ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ለብይን ተቀጠረ
- ክሳቸው ከሌሎች ተከሳሾች እንዲነጠልላቸው ጠየቁ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ሁከትና ብጥብጥ በማባባስ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍና የሐሰት ወሬዎችን በማውራት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ያቀረቡት...
View Articleማዕድን ሚኒስቴር የአላና ፖታሽ ፕሮጀክትን መረከብ አልቻለም
የማዕድን፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አላና ፖታሽ አፋር አቋርጦ የወጣውን የፖታሽ ማዕድን ልማት ፕሮጀክት ሊረከብ አለመቻሉን ገለጸ፡፡የማዕድን፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ቴዎድሮስ ገብረአብ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አላና ፖታሽ አፋር ያሉበትን የታክስ ግዴታዎች ተወጥቶ ከግብር ነፃ...
View Articleየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስተጓጎልና ነዳጅ እንዳዳይገባ ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 77 ግለሰቦች ተከሰሱ
- በክሱ 12 ኤርትራውያን ተካተዋልየሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ እንዳይሆንና ነዳጅ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለማድረግ፣ በኤርትራ ሥልጠና ወስደው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉ 77 ግለሰቦች ክስ...
View Articleየፖለቲካ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር ውይይት ቀጥሏል
ገዢው ፓርቲን ጨምሮ ከጥቂት ሳምንት በፊት የቅድመ ድርድር ውይይት የጀመሩት 22 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዓርብ የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ውይይት አደረጉ፡፡ በውይይቱ ወቅት አሁንም ያልተፈቱ ልዩነቶች ተንፀባርቀዋል፡፡ውይይቱን የመምራት ኃላፊነት ለገዢው ፓርቲ ተሰጥቶ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በመሩት የዓርቡ...
View Articleበአራዳ ክፍለ ከተማ የተለያየ ኃላፊነት የነበራቸው ሠራተኞች ላይ የሙስና ክስ ተመሠረተ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የነበሩ ስምንት ሠራተኞች የሙስና ክስ ተመሠረተባቸው፡፡የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሙስና ተግባር ወንጀል ፈጽመዋል ብሎ ክስ የመሠረተባቸው፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ናቸው፡፡...
View Articleአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በስም ማጥፋት ከሰሰ
- ዩኒቨርሲቲው 200 ሺሕ ብር የሞራል ካሳ ጠይቋልአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለዓመታት የኦዲት ሒሳብ አለማከናወኑን የሚያትቱ ዘገባዎች በ2007 እና 2009 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሁለት ጊዜ በመታተማቸው፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትንና የጋዜጣውን አዘጋጅ በስም ማጥፋት ክስ መሠረተባቸው፡፡ እንዲሁም የሐበሻ...
View Articleመንግሥት በጥጥ ኤክስፖርት ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ አነሳ
መንግሥት በአገሪቱ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የሚያስፈልጋቸውን ጥጥ በቀላሉ እንዲያገኙ ለማድረግ፣ በአገር ውስጥ የጥጥ ምርት ኤክስፖርት ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ አነሳ፡፡የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የካቲት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጻፈው ደብዳቤ፣ ከዚህ...
View Articleየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ የታሳሪዎችን መብት እየጣሰች ነው አለ
እ.ኤ.አ. በ2016 በኢትዮጵያ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ይዞታ የዳሰሰው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት በዓመቱ ለእስር የተዳረጉ ከ10,000 በላይ ዜጎች ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ፣ የሕግ ማማከር አገልግሎት እንዳላገኙና ክስ እንዳልተመሠረተባቸው ገለጸ፡፡ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሰኔ ወር...
View Articleበደመወዝ ጭማሪው ባልተገባ መንገድ ለማትረፍ በሚሞክሩ ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በመደረጉ ሳቢያ በአንዳንድ የምግብ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን፣ ከዚህ በኋላም ዕርምጃ እንደሚወስድ ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በቅርቡ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ያልተገባ የዋጋ ጭማሪዎች...
View Articleበሶማሌና በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ለቀጠለው ግጭት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጨፌው ወሰነ
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ መደበኛ ጉባዔውን ያካሄደው የኦሮሚያ ክልላዊ ምክር ቤት (ጨፌ) የኦሮሚያ መንግሥት በሶማሌና በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች በቀጠለው ግጭት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ወሰነ፡፡ምክር ቤቱ ባካሄደው ጉባዔ ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ ከነበሩ ጉዳዮች የላቀ ትኩረት የተሰጠው፣ ላለፉት አራት ወራት የቀጠለው...
View Article